የተለያዩ
በሊቢያ የባህር ዳርቻ በደረሰ አደጋ የሁለት ጨቅላ ህፃናት ህይወት ጨምሮ 53 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 03/06/2018፡- በሊቢያ የባህር ዳርቻ ላይ በደረሰ የጎማ ጀልባ መገልበጥ አደጋ የሁለት ጨቅላ ህፃናትን ህይወት ጨምሮ 53 ሰዎች መሞታቸውና መጥፋታቸው ተረጋገጠ።
በጀልባዋ ላይ ከነበሩ 55 ሰዎች መካከል 53ቱ የደረሱበት አልታወቀም፤ አልያም ህይወታቸው አልፏል።
በአደጋው ህይወታቸውን ካጡት መካከል ሁለት ጨቅላ ህፃናት ይገኛሉ።
ከሞት የተረፉት 2 ሰዎች ብቻ ሲሆኑ፣ በአሁኑ ወቅት የድንገተኛ ህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።
እንደ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት መግለጫ ከሆነ፣ ጀልባዋ ረቡዕ ምሽት 5 ሰዓት ላይ ከዛውያ ተነስታ ለስድስት ሰዓታት ያህል እንደተጓዘች በዙዋራ የባህር ዳርቻ አካባቢ ተገልብጣለች።
ተጓዦቹ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተሰባሰቡ ስደተኞች እንደነበሩ ተገልጿል።
የመካከለኛው ሜዲትራኒያን የጉዞ መስመር አሁንም እጅግ ገዳይ ሆኖ የቀጠለ ሲሆን በፈረንጆቹ 2026 መጀመሪያ ላይ ብቻ 484 ስደተኞች መሞታቸው ወይም መጥፋታቸው ተመዝግቧል።
በጥር ወር ብቻ በከባድ የአየር ሁኔታ ምክንያት በደረሱ አደጋዎች የ375 ሰዎች ህይወት ማለፉን ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አስታውቋል።


