
ኢትዮ ሞኒተር፡ 29/05/2018፡- የዛሬው ውይይት ስኬታማ ከሆነ አገራቱ መደራደር የሚችሉባቸው ነጥቦች ላይ ይስማማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ኢራን የኒውክሌር ፕሮግራሟን እንድታቋርጥ የምትፈልገው አሜሪካ፤ አገሪቱ ያከማቸችውን ዩራንየም እንድታስወግድም ጠይቃለች።
የኢራን ባለስቲክ ሚሳዔል እና ለቀጣናው ታጣቂዎች የምታደርገው ድጋፍ የውይይቱ አካል እንዲሆን አሜሪካ ትፈልጋለች።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ የድርድሩን ውጤት እየተጠባበቁ መሆኑን ጽሕፈት ቤታቸው አስታውቋል።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ዛሬ አርብ ኦማን ውስጥ በሚደረገው ድርድር ከስምምነት ሊደረስ ይችል እንደሆነ ለመወሰን ሂደቱን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቅርበት እንደሚከታተሉ ተነገረ።
የዋይት ሐውስ ቃል አቀባይ ካሮላይን ሌቬት፡ ኦማን መስካት ውስጥ ድርድሩ ከመጀመሩ በፊት ሐሙስ ሌሊት በሰጡት መግለጫ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከንግግሩ ውጤት እንደሚጠብቁ አመልክተዋል።
ስለዚህም ፕሬዝዳንት ትራምፕ የመካከለኛው ምሥራቅ ልዩ ተወካያቸውን ስቲቭ ዊትኮፍ እና የልጃቸውን ባል ጃሬድ ኩሽነርን ለድርድር ልከዋል በማለት “ውጤቱ ምን ሊሆን እንደመችል የምናየው ነው። ፕሬዝዳንቱ ከተደራዳሪዎቻቸው ውጤቱን ለመስማት እየተጠባበቁ ነው።”
ይህ በእንዲህ እያለ አሜሪካ ከኢራን ጋር የምታደርገው ድርድር ከመጀመሩ በፊት ዜጎቿ ኢራንን ለቅቀው እንዲወጡ አዘዝዛለች።
በአሜሪካ እና በኢራን መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል ኦማን ውስጥ የሚደረገው የመጀመሪያው ንግግር ሰዓታት ሲቀሩት የአሜሪካ ዜጎቿ ከኢራን ለቅቀው እንዲወጡ አስጠነቀቀች።



