አውሮፓ
ዩክሬን በጦርነቱ ምክንያት 55,000 ወታደሮች እንደተገደሉባት አስታወቀች።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 29/05/2018፡- የዩክሬይኑ ፕሬዝደንት ዘለንኪ ዛሬ ጦርነቱ ያስከፈለውን የሰው ህይወት ዋጋ ይፋ አድርገዋል፡፡
በዚህ ጦርነት በጠቅላላው 55,000 ወታደሮቻቸው መሞታቸውን ቢገልፁም ከሩሲያ በኩል ግን ቁጥሩ ከፍ ያለ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
እንደፕሬዝደንቱ ገለፃ ዩክሬይን ባለፈው አመት ብቻ የተገደሉባት ወታደሮች ቁጥር 9 ሺህ ሲሆን ይህንንም ለወር አካፍለው በአንድ ወር ውስጥ 750 ወታደሮችን ማጣታቸውን ገልፀዋል፡፡
ይሁንና ባለፈው ወር ብቻ 35,000 የሩሲያ ወታደሮች መገደላቸውን የጠቀሱት ዘለንስኪ ይህንንም በሂሳብ ስሌት ውስጥ ሲያሰሉት ለአንድ የዩክሬይን ወታደር 47 የሩሲያ ወታደሮች እንደሚሆን አስታውቀዋል፡፡
ሲናገሩም ‹‹እኛ በእያንዳንዱ ሜትርና ኪሎ ሜትር መሬታችን ምን ያህል የሩሲያ ወታደሮች እየከሰሩ መሆኑን በሚገባ እናውቃለን፡፡ እነሱ የሚሞቱን ሰዎች አይቆጥሩም፡፡ እኛ ግን ለመቁጠር እንደገደዳለን›› ብለዋል፡፡
ፕሬዝደንቱ ጨምረውም ሩሲያ ምስራቃዊ ዩክሬይንን ለመቆጣጠር ተጨማሪ 800,000 ወታደሮችን ማጣት እንደሚጠበቅባት ገልፀው ይህም የሚሆነው በጣም ቀርፋፋ በሆነ ሂደት እንደሆነና ቢያንስ ሁለት አመት እንደሚፈጅ አስታውቀዋል፡፡



