ኢኮኖሚ

“በየካቲት ወር ነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል”

ኢትዮ ሞኒተር፡ 28/05/2018፡- በየካቲት ወር “ከአውሮፕላን ነዳጅ በቀር የሌሎች ነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል” ሲል የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

የቤንዚን፣ የነጭ ናፍጣ፣ የኬሮሲን፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣ እና የከባድ ጥቁር ናፍጣ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር ሲሸጥበት በነበረው እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያስቀመጠው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ከጥር 27 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት 12:00 ሰዓት ጀምሮ ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል።

ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር የሌሎች የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ የመሸጫ ዋጋ በጥር በነበረበት ይቀጥላል ተብሏል።

የአውሮፕላን ነዳጅ የችርቻሮ መሽጫ ዋጋ በአዲስ አበባ ከተማ 136.80 ብር/በሊትር እንዲሆን በመንግሥት መወሰኑንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

አሁን ላይ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ የቤንዚን 129.12 ብር በሊትር፣ ነጭ ናፍጣ 129.12 ብር በሊትር፣ ኬሮሲን 129.12 ብር በሊትር መሆኑን ይታወቃል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates