ዲፕሎማሲ
የሶማሊላንድ መሪ ወደ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ማቅናታቸው ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 26/05/2018፡- ሶማሊላንድ የቀጠናው ጉዳዮች እየጨመሩ ሲሄዱ የበለጠ ትስስር ትፈልጋለች ተብሏል።
የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዱራህማን መሀመድ አብዱላሂ ዛሬ ማክሰኞ ወደ ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ማቅናታቸው ተገልጿል።
ፕሬዝዳንቱ የካቢኔ ሚኒስትሮችን እና ከፍተኛ አማካሪዎችን ያካተተ ከፍተኛ ደረጃ ያለው ልዑክ በመምራት አቡዳቢ መግባታቸው ጽህፈት ቤታቸው አስታውቋል።
ጉዞው ከኢሚሬትስ መንግስት በይፋ የቀረበለትን ግብዣ ተከትሎ ሲሆን ፕሬዝዳንት አብዱራህማን መሀመድ በልማት እና በመንግስታት መካከል ትብብር ላይ ያተኮረ ኮንፈረንስ ላይ እንደሚገኙ ይጠበቃል።
ባለስልጣናቱ በአቡዳቢ ከከፍተኛ የኢሚሬትስ መሪዎች ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ለማጠናከር እንደሚወያዩም ተናግረዋል።
ውይይቱ በልማት ፕሮጀክቶች እና ኢንቨስትመንት ላይ ያተኩራል ተብሎ ይጠበቃል፤ ይህም ኢሚሬትስ በሶማሊላንድ ኢኮኖሚ ውስጥ የጀመረችውን ጉልህ ሚና ለማጠናከር እንደሆነ እየተገለፀ ነው።
ኢሚሬትስ ከሶማሊያ የነበራትን ግንኙነት ከተቋረጠ በኃላ ፊቷ ወደ ሶማሊላንድ ያዞረች ትመስላለች።



