ፖለቲካ
እስካሁን 41 በተናጠል እና 15 በሦስት የተለያዩ ጥምረቶች የቀረቡ ፓርቲዎች ዕጩዎቻቸውን ማስመዝገባቸው የምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፀጥታ ሁኔታን ለመገምገም ያለመ መድረክ ተካሄደ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 25/05/2018፡- ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ያለውን የፀጥታ ሁኔታ ለመገምገም ያለመ መድረክ ዛሬ ጥር 25 ቀን 2018 ዓ/ም ሲካሄድ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ተገልጿል።
ከጥር 1 ጀምሮ እስከ የካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም በሚቆየው የዕጩዎች ምዝገባ እስካሁን 41 በተናጠል እና 15 በሦስት የተለያዩ ጥምረቶች የቀረቡ ፓርቲዎች ዕጩዎቻቸውን በመመዝገብ ላይ መሆናቸውን የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ኃይሉ ተናግሯል።
ምርጫው በሚደረግባቸው አካባቢዎች ያለውን የፀጥታ ሁኔታ በአረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ የተለየ ሲሆን÷ እነዚህ የፀጥታ ሪፖርቶች በመድረኩ ቀርበው ከባለድርሻ አካላት ግብአት እንደተሰበሰበባቸው ታውቋል።
የፀጥታ ሁኔታ ተለዋዋጭ እንደመሆኑ በአንድ መድረክ ብቻ እንደማይቋጭ የጠቀሱት ሰብሳቢዋ÷ በየጊዜው በሚኖሩ አዳዲስ ሁኔታዎች ተመስርቶ ለምርጫው የሚደረገው ዝግጅት እንደሚቀጥል ተናግረዋል።



