በሶማሊያ ፓርላማ እንደገና ብጥብጥ ተነሳ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 25/05/2018፡- ፖሊስ ወደ ፓርላማ አዳራሹ ጥሶ መግባቱና የፓርላማ አባላት መጎዳታቸውም ተሰምቷል።
ዛሬ በሶማሊያ ፓርላማ ለሁለተኛ ጊዜ በተከሰተው ረበሻ ፖሊስ ወደ ምክር ቤቱ የገባ ሲሆን በተቃዋሚዎች ጉዳት መድረሱ የአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።
በሕገ መንግስቱ ማሻሻያ ዙሪያ ለመወያየት የተጠራው ምክር ቤት በሐሳብ ሳይግባባ በመቅረቱ ብጥብጥ የተፈጠረ ሲሆን የታችኛው ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፖሊስ በማጥራት የፑንትላንድ እና የጁባላንድ ተቃዋሚዎች እንዲወጡ መደረጋቸው በዚህ ሂደት ግን የሕግ አውጪ አባል መቁሰላቸው የዐይን እማኞች ተናግሯል።
ባለፈው ሳምንት ተመሳሳይ ብጥብጥ ያስተናገደው የሶማሊያው ፓርላማ አፈ ጉባኤው 18 የፓርላማ አባላት ከስብሰባው እንዲታገዱ አድርጓል።
ዛሬ በተቃዋሚ የፓርላማ አባላት እና በአፈ ጉባኤው በተፈጠረው ረበሻና የፊስካ መንፋት ተቃውሞ ግጭትና ትርምስ ከተፈጠረ በኋላ፣ ሕግ አውጪዎች ፖሊሶችን አሸንፈው ከምክር ቤቱ እንዲወጡ አስገደዷቸው፣ ይህም በታቀዱት የሕገ መንግሥት ለውጦች ላይ በተነሳው አለመግባባት መካከል ውጥረት እንዲፈጠር አድርጓል።
ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃመድ በስፋት አወዛጋቢ የሆኑ የሕገ መንግሥት ለውጦችን ለማራመድ እየሞከሩ ባሉበት ወቅት ከፑንትላንድ እና ከጁባላንድ የተውጣጡ የፓርላማ አባላት ወደ ፓርላማ እንዳይገቡ በመከልከላቸው በሞቃዲሾ ስጋቶች አንዣብቧል።
ሕግ አውጪዎች የጸጥታ ኃይሎች ይህንን ለማድረግ ሙሉ ሥልጣን እንዳላቸው በመቃወማቸው በፖሊስ ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው እንደሆነ ገልጿል።
“እንገድላችኋለን፣ እንተኩስባቸዋለን’ ብሎናል” ሲሉ ወደ ፓርላማ እንዳይገቡ ከተከለከሉ በኃላ አንድ የሶማሊያ የፓርላማ አባል ተናግሯል።
የብጥብጡ መነሻ ምክንያት የሕገ መንግስቱ ማሻሻያ የአንድ ወገን ፍላጎት ለሟሟላት የተደረገ ነው የሚል ነው።



