መካከለኛ ምስራቅ

በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የተካሄደው ድርድር ያለውጤት መጠናቀቁ ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 18/05/2018፡- በሩሲያ፣ በዩክሬን እና በአሜሪካ መካከል በኢሚሬትስ የተደረገው ንግግር ውጤት አላስገኘም ተብሏል።

አቡ ዳቢ ውስጥ የተካሄደው ሩሲያ፣ ዩክሬን እና አሜሪካ የተሳተፉበት የመጀመሪያው የሦስትዮች የሰላም ንግግር ተጨባጭ ውጤት ሳያስገኝ መጠናቀቁ መረጃዎች ጠቁሟል።

አቡ ዳቢ ውስጥ የተካሄደው ንግግር ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወረራ ከጀመረች ከአራት ዓመት በኋላ የተካሄደ የመጀመሪያው የሦስትዮሽ ውይይት ነው።

ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ በኤክስ ገፃቸው እንዳሰፈሩት የንግግሩ “ዋነኛ ትኩረት ጦርነቱን ለማቆም በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምከር ነበር” ብለዋል።

አክለውም ሁሉም ወገኖች ወደ አገሮቻቸው ተመልሰው ከመሪዎቻቸው ጋር በመመካከር ለቀጣይ ውሳኔዎች እንዲዘጋጁ ከስምምነት መደረሱን አመልክተዋል።

ስማቸው ያልተጠቀሰ አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን ቀጣዩ ዙር ንግግር በሚቀጥለው ሳምንት እሁድ አቡ ዳቢ ውስጥ እንደሚካሄድ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ለሁለት ቀናት የተካሄደው ንግግር ያበቃው ሩሲያ ክፉኛ የተጎዳውን የዩክሬን የኃይል ማመንጫ መሠረተ ልማቶችን ዒላማ አድርጋ ከባድ የአየር ጥቃቶችን ከፈጸመች በኋላ ነው።

የዩክሬን ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት በጥቃቱ አንድ ሰው ሲገደል ሌሎች 35 ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በሩሲያ በኩል ደግሞ በምትቆጣጠረው የዩክሬን አካበቢ በአምቡላንስ ላይ በተፈጸመ ጥቃት ሦስት የሕክምና ባለሙያዎች ተገድለዋል ስትል የዩክሬን ኃይሎችን ከስሳለች።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates