ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ አየር ኃይል የተመሰረተበት 90ኛ ዓመቱ ዛሬ ማክበር ጀመረ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 15/05/2018፡- የኢትዮጵያ አየር ኃይል፣ ከምስረታው ጀምሮ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በማስከበርና ሕዝብን በማገልገል ላይ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን ዘጠኝ አሥርት ዓመታትን የተሻገረው ይህ አንጋፋ ተቋም፣ ዛሬም ብቁ ባለሙያዎችን እያፈራ እንደሚገኝ ይነገራል፡፡

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ለተቋሙ ግንባታ በተሰጠው ከፍተኛ ትኩረት፣ አየር ኃይሉ ኢትዮጵያን በሚመጥን መልኩ ዘመናዊነትን ተላብሶ በርካታ ስኬቶችን እያስመዘገበ እንደሚገኝ እና ተቋሙ 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን “የኢትዮጵያ አየር ኃይል የነፃነትና የአንድነት ምልክት” በሚል መሪ ሀሳብ ከዛሬ ጥር 15 እስከ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ መርሐ ግብሮች እያከበረ እንሚያከብር ተመላክተዋል።

አየር ኃይሉ በአሁኑ ወቅት ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ አስተዋጽኦ ማድረግ የሚያስችል ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝም ተገልፀዋል፡፡

አየር ኃይሉ ባለፉት 90 ዓመታት ውስጥ በርካታ ድሎችን በመጎናጸፍ ለኢትዮጵያ አንድነት እና ሉዓላዊነት መከበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱንም፣ ከጊዜው ጋር የሚጓዝ የሠለጠነ የሰው ኃይል በማሰማራት አሁን ላለበት ከፍተኛ የዕድገት ደረጃ መድረስ መቻሉን የተገኙ መረጃዎች ያሳያሉ።

የኢፌዴሪ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የኢትዮጵያን ገጽታ በሚያጎላ መልኩ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates