መካከለኛ ምስራቅ

የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ የሩሲያ፣ የዩክሬን እና የአሜሪካ ተደራዳሪዎችን ያካተተ ወሳኝ ስብሰባ ለመስተናገድ በዝግጅት ላይ መሆንዋን ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 15/05/2018፡- መድረኩ ሞስኮ በዩክሬን ላይ የጀመረችው ሙሉ ወረራ ወደ አራት ዓመታት ገደማ ከጠጋ ወዲህ፣ ሦስቱም ሀገራት በአንድ ላይ የሚሳተፉበት የመጀመሪያው ስብሰባ ነው ተብለዋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ሁለቱን መልዕክተኞቻቸውን ስቲቭ ዊትኮፍን እና ጃሬድ ኩሽነርን ወደ ስፍራው ልከዋል።

እነዚህ መልዕክተኞች ወደ ኤሚሬትስ ያመሩት ሌሊቱን በሞስኮ ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ መሆኑ ተገልጿል።

ዩክሬን በበኩሏ የብሔራዊ ደህንነት እና መከላከያ ምክር ቤት ኃላፊ ሩስተም ኡሜሮቭን፣ የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ ኪሪሎ ቡዳኖቭን፣ ተደራዳሪው ዴቪድ አራካሚያን እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ አንድሬ ህናቶቭን ጨምሮ ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ልካለች።

በሩሲያ በኩል የልዑካን ቡድኑን የሚመሩት የሀገሪቱ ወታደራዊ የስለላ ተቋም ዳይሬክተር የሆኑት ጄኔራል ኢጎር ኮስትዩኮቭ ናቸው።

በተጨማሪም የሩሲያ የኢንቨስትመንት መልዕክተኛ ኪሪል ዲሚትሪቭ በስፍራው የሚገኙ ሲሆን፣ ከአሜሪካው መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ጋር በተናጠል በጎንዮሽ ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ምንም እንኳን ልዑካኑ በስፍራው ቢገኙም፣ የአሜሪካ፣ የሩሲያ እና የዩክሬን ተደራዳሪዎች በአካል በአንድ ክፍል ውስጥ ሆነው በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ ይነጋገሩ እንደሆነ እስካሁን ግልጽ መረጃ አልወጣም።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ባለፈው ወር እንደተናገሩት፣ አሜሪካ ያቀረበችው ባለ 20 ነጥብ የሰላም እቅድ 90 በመቶ ዝግጁ ቢሆንም፣ በተለይ በመሬት ይዞታ ጉዳይ ላይ አለመግባባቶች አሁንም አሉ።

የክሬምሊን አማካሪ ዩሪ ኡሻኮቭ የአሜሪካ ልዑካን በሞስኮ ያደረጉትን ቆይታ “በሁሉም ረገድ ጠቃሚ” ሲሉ ቢገልጹትም፣ በፑቲን እና በአሜሪካውያኑ መካከል ምን እንደተወራ እና ይህ ለዛሬው ስብሰባ ምን አንድምታ እንዳለው የታወቀ ነገር የለም።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates