ፖለቲካ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ፣ አሜሪካን ወቀሱ ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 12/05/2018፡- ዋና ጸሐፊው ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ አሜሪካ ዓለም አቀፍ ሕጎችን ከመከተል ይልቅ ለራሷ ኃይል እና ጉልበት ቅድሚያ እየሰጠች ነው ሲሉ ወቅሷል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተመድን ውጤታማነት እና ዓላማ አስመልክተው ለሰነዘሩት ትችት ምላሽ የሰጡት ጉተሬዝ፣ ድርጅታቸው እንደ አሜሪካ ባሉ “ታላላቅ ኃያላን” ሀገራት ላይ ዓለም አቀፍ ሕግን የማስከበር አቅም እንደሌለው አምነዋል።

“የሕግ የበላይነት (Power of law) በጉልበት የበላይነት (Law of power) መተካት አለበት ብለው የሚያምኑ አሉ” ያሉት ዋና ጸሐፊው፣ “የአሜሪካን ወቅታዊ ፖሊሲ ሲመለከቱ፣ ዘላቂ የሆኑ የጋራ መፍትሄዎች ፋይዳ እንደሌላቸው እና ዋናው ነገር የአሜሪካን ጉልበትና ተፅዕኖ መጠቀም ነው የሚል ጠንካራ እምነት እንዳለ በግልጽ ይታያል” ብለዋል።

አያይዘውም አሜሪካ አንዳንዴ ከዓለም አቀፍ ሕግ ይልቅ የራሷን ጉልበት እንደ መለኪያ እንደምትጠቀም ተናግረዋል።

ጉተሬዝ በቃለ ምልልሳቸው የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ወቅታዊውን የዓለም እውነታ የማይወክል እና ውጤታማነቱን ያጣ መሆኑን ተናግረዋል።

በተለይም አምስቱ ቋሚ አባል ሀገራት (አሜሪካ፣ ሩሲያ፣ ቻይና፣ እንግሊዝ እና ፈረንሳይ) ያላቸው የድምፅን በድምፅ የመሻር መብት፣ ሀገራቱ የራሳቸውን ጥቅም ብቻ እንዲያራምዱ እድል እንደሰጣቸው ጠቁመዋል።

ዋና ጸሐፊው ምክር ቤቱ ተቀባይነት እንዲኖረው እና የመላው ዓለም ድምፅ እንዲሆን ከተፈለገ፣ የአባላት አወቃቀሩ መሻሻል እና የቪቶ አጠቃቀም ሊገደብ እንደሚገባም ምክረ-ሀሳብ አቅርበዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates