መካከለኛ ምስራቅ

በኢራን ኢንተርኔት ከተቋረጠ 180 ሰዓታት አለፉ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 08/04/2018፡- ኔት ብሎክስ የተሰኘውና በዓለም የኢንተርኔት ስርጭትን የሚከታተለው ድርጅት በኢራን የኢንተርኔት አገልግሎት ከተቋረጠ 180 ሰዓታት ማለፉን አስታወቀ።

ድርጅቱ በኤክስ ገጹ ላይ ባሰፈረው መልዕክት አገሪቱ አሁን ያጋጠማት እአአ በ2019 ከነበረው የኢንተርኔት መቆራረጥ የበለጠ መሆኑን ገልጿል።

በኢራን ከሁለት ሳምንት በላይ የቀጠለ ሕዝባዊ አመጽ እየተካሄደ ነው።

አመፁ የተቀሰቀሰው የኑሮ ውድነትን ምክንያት አድርጎ ቢሆንም አገሪቱን ለረዥም ዓመታት ያስተዳደረው መንግሥት ከሥልጣን እንዲወርድ የሚጠይቁ ድምጾች ተሰምተዋል።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች መንግሥት ተቃውሟቸውን ለመግለጽ አደባባይ በወጡ ኢራናውያን ላይ በወሰደው እርምጃ ከ2400 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ገልጸዋል።

ኔት ብሎክስ እአአ በ2019 ለአንድ ሳምንት ያህል የዘለቀውን የኢንተርኔት መቋረጥ ጠቅሶ መንግሥት የወሰደው እርምጃ ምን ያህል የከፋ እንደነበር የታወቀው ኢንርኔት ዳግም ሲጀመር ነው ብሏል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates