ፖለቲካ
ኡጋንዳ የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከመካሄዱ ጥቂት ቀናት በፊት የኢንተርኔት አገልግሎት ዘጋች፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 06/04/2018፡- ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ የ40 ዓመት የስልጣን ዘመናቸውን እንደሚያራዝሙ በሚጠበቀው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከመድረሱ ጥቂት ቀናት በፊት በመላ አገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎት መዘጋትዋ ታውቀዋል፡፡
የመንግስት የቁጥጥር አካል የሞባይል ኔትወርክ ኦፕሬተሮች ማክሰኞ ከምሽቱ 6 ሰዓት ጀምሮ የህዝብ ኢንተርኔት አገልግሎትን እንዲዘጉ መመሪያ ሰጥቷል።
የኢንተርኔት ሞኒተር ኔትብሎክስ በኋላ ላይ “በሀገር አቀፍ ደረጃ የኢንተርኔት ግንኙነት መቋረጡን” አረጋግጧል።
የኔትወርክ መቆራረጡ ነገ ጥር 15 የሚካሄደውን ሃገራዊ ምርጫ የ81 ዓመቱ ሙሴቬኒ የአፍሪካ ሶስተኛው ረጅም ጊዜ የስልጣን መሪ ለማድረግ የተደረገ ቅድመ ማጭበርበር እንደሆነ ተቃዊሚዎች እገለፁ ይገኛሉ፡፡



