ኢኮኖሚ

የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ገጠመኝ አለ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 04/04/2018፡- የገጠመው የገንዘብ እጥረት ለመቅረፍ የሚያስችለው ደንብ እንዳፀደቀ የገለፀው አስተዳደሩ ከመንግስት ሰራተኞች እና የንግድ አከፋፋዮች መዋጮ እንደሚሰበስብ አስታውቋል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ሥራ አስፈፃሚ አሁን ያሉትን ችግሮች ለመፍታት ሀብት ለማሰባሰብ የሚያስችል ደንብ እንዳፀደቀ የገለፀ ሲሆን ይህም ጥር 1/2018 ተብሎ እንደሚጠራ ተገሎልጿል።

የሀብት ማሰባሰቢያ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ፣ ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ ምንም አይነት የማገገሚያ ሥራ እንዳልተከናወነ በመናገር ከጥቅምት ወር ጀምሮ የትግራይ በጀት ተከልክሏል፤ አንድ ሶስተኛው በጀት ብቻ ነው እየመጣ ያለው ብለዋል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከፍተኛ የበጀት ጉድለት እያጋጠመው በመሆኑ የጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው የትግራይ አርበኞች በከባድ ስቃይ ላይ ናቸው፤ እንዲጠብቁም ልንነግራቸው አንችልም ሲሉ ተደምጧል።

ተፈናቃዮቹ በስምምነቱ መሰረት እንዲመለሱ ከተፈለገ፣ ሀብት ያስፈልገዋል፤ ድጋፍም ያስፈልጋቸዋል ያሉት ዶ/ር አብርሃም የማገገሚያ ሥራ ለማስጀመር ሀብት ማሰባሰብ አለብን ብለዋል።

በ17 ባንኮች ውስጥ አካውንቶች እንዲከፈቱ መጠየቃቸውን እና እስካሁን ከ13 ባንኮች ምላሽ እንደሰጡ የተገለፀ ሲሆን የሀብት ማሰባሰቡን የሚመሩ ወደ ሰባት የሚጠጉ ንዑስ ኮሚቴዎች እንደተቋቋሙ ተገልጿል።

በ2017 የበጀት ዓመት ዓመታዊ ሽያጭ ላይ በመመስረት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ምንጩ እና መጠኑ በሁሉም ንግዶች እንደሚከፈል የተገለፀ ሲሆን ከአምራቾች እና አከፋፋዮች የሚመጡ የአልኮል፣ ለስላሳ መጠጦች እና የታሸገ ውሃ ዋጋዎችን በመጨመር ከአንድ ጠርሙስ ቢራ 3 ብር፣ ከለስላሳ ጥርሙዝ 1 ብር፣ ከአንድ ጠርሙስ ቮድካ 10 ብር፣ ከአንድ ጠርሙስ ወይን 20 ብር፣ ከጠርሙስ ዊስኪ 200 ብር፣ ከታሸገ ውሃ በደርዘን 12 ብር እና ከ20 ሊትር 20 ብር እንደሚሰበሰብ ኮሚቴው አስታውቋል።

እንዲሁም ከአንድ ኩንታል ሲሚንቶ 100 ብር ይሰበሰባል የተባለ ሲሆን የሲቪል ሰራተኞች፣ የፍትህ አካላት፣ የደህንነት ኃይሎች እና የፖሊስ፣ የግል እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሰራተኞች በስምምነት ከተጣራ ወርሃዊ ደሞዛቸውን እንዲያዋጡ እንደሚደረግ ተገልጿል።

የገቢ መሰባሰቢያው መርሃ ግብር ጥር 13 በሚካሄደው ብሔራዊ ኮንፈረንስ ይፋ እንደሚሆን ታውቋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates