የተለያዩ

የፌዴራል ፖሊስ ከ14 ቢሊዮን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ከ729 ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስታወቀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 04/04/2018፡- ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽንና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ከ14 ቢሊየን 51 ሚሊየን 586 ሺህ ብር በላይ የዋጋ ግምት ያላቸው የገቢና ወጪ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ከ729 ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ኮ ጀነራል መላኩ ፋንታ ገለፁ።

ምክትል ኮሚሽነሩ ይህን የገለፁት በጠቅላይ መምሪያው በተካሄደው የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወር የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ላይ ነው።

በዚሁ ወቅት ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል በተሰራው ሥራም ከ1ሺህ 6 መቶ በላይ አገር ጥለው ሊሄዱ የነበሩ ሰዎች  ተይዘው ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱ የተደረገ መሆኑን የገለፁት ም/ኮሚሽነሩ በተጨማሪም 41 አስኮብላዮችም በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል።

አክለውም በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ “የሽብር ቡድኖችን” እኩይ ዓላማ በማክሸፍ፤ በደቡብ፣ በጋምቤላ፣ በአፋር እና በሱማሌ ክልሎች የተከሰቱ ግጭቶችን በመቆጣጠር ረገድ ጉልህ ድርሻ ተወጥቷል ብለዋል።

እንዲሁም በአገሪቱ በሁሉም አካባቢዎች ያሉ 625 ግዙፍ ተቋማትና ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም ታላላቅ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶችን በመጠበቅ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡ በግምማው ተነስቷል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates