ኢኮኖሚ
የኤርትራ ኢኮኖሚ ለመጀመሪያ ጊዜ በመረጃ ተደግፎ ይፋ ሆነ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 04/04/2018፡- በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ ዓመት በ3.8 በመቶ እንዳደገም መረጃው አሳይቷል።
የኤርትራን ኢኮኖሚ የሚያሳዩ መረጃዎች እንብዛም አይታወቁም ነበር።
ምክንያቱ ደግሞ ኤርትራ የአለምን ኢኮኖሚ ለሚተነትኑና ለሚሰንዱ አካላት በሯን ዝግ ማድረጓ ነው፡፡
ነገር ግን በዚህ ሳምንት ባልተለመደ ሁኔታ ያለፈው የፈረንጆች አመት ማለትም 2025 የኤርትራ ኢኮኖሚ ምን እንደሚመስል የሚያሳይ ሪፖርት ወጥቷል፡፡
ይህ ሪፖርት እንደሚገልፀው በ2025 የኤርትራ ህዝብ ብዛት 3.6 ሚሊዮን ሲሆን አመታዊ የህዝቧ መጠን የሚጨምረው ደግሞ በ1.8 በመቶ ነው፡፡
ከህዝቧ ውስጥ ወደ 20 በመቶ ገደማው የኢንተርኔት ተጠቃሚ መሆኑን የገለፀው ሪፖርቱ አመታዊ የዋጋ ግሽበቱ ደግሞ 1.3 በመቶ መሆኑን ያስረዳል፡፡
ኤርትራ በዋነኝነት ወደውጭ የምትልካቸው የቀንድ ከብቶች፣ ማሽላ፣ ጨርቃጨርቅና ምግብ መሆኑን የጠቀሰው ሪፖርቱ የምርቷ ዋነኛ ተቀባዮችም ጣሊያን፣ ሱዳን፣ ሳኡዲ አረቢያ፣ ቻይና፣ ዩናይትድ ኪንግደምና ግብፅ መሆናቸውን አስታውቋል፡፡
ከውጭ ከምታስገባቸው ውስጥ ማሽኖች፣ ነዳጅና ምግብ ዋናዎቹ መሆናቸውን ገልፆም የአገሪቱ አመታዊ ምርት እድገት 3.8 በመቶ ነው ብሏል፡፡
በወጪና ገቢ ምርት መካከል ያለው ልዩነት ደግሞ ኔጋቲቭ 0.089 ቢሊዮን ዶላር መሆኑን አስረድቷል፡፡



