መካከለኛ ምስራቅ

በኢራን በተቀሰቀሰው ተቃውሞ የሟቾች ቁጥር ከ500 በላይ መድረሱን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አስታወቀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 04/04/2018፡- ትራምፕ ጣልቃ የሚገቡ ከሆነ ቴህራን የአሜሪካን የጦር ሰፈሮች ኢላማ እንደምታደርግ ዝታለች።

በኢራን በተቀሰቀሰው ተቃውሞ 490 ተቃዋሚዎች እና 48 የጸጥታ ኃይሎች መሞታቸውን በአሜሪካ የሚገኝ አንድ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን እሁድ ዕለት አስታወቀ።

በሌላ በኩል ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለተቃዋሚዎች ድጋፍ ለመስጠት ጣልቃ ለመግባት ያሰሙትን ማስጠንቀቂያ ተግባራዊ የሚያደርጉ ከሆነ፣ ቴህራን የአሜሪካን የጦር ሰፈሮች ኢላማ እንደምታደርግ ዝታለች።

የኢስላማዊ ሪፐብሊክ ኃይማኖታዊው አስተዳደር ከጎርጎሮሳውያኑ 2022 ወዲህ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ እያጋጠመው ይገኛል።

ትራምፕ በበኩላቸው በተቃዋሚዎች ላይ የኃይል እርምጃ የሚወሰድ ከሆነ ጣልቃ እንደሚገቡ በተደጋጋሚ አስጠንቅቀዋል።

መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ህራና በኢራን ውስጥና ከውጭ ካሉ አክቲቪስቶች አገኘሁት ባለው ወቅታዊ መረጃ መሠረት፤ በሁለት ሳምንታት ተቃውሞ የ490 ተቃዋሚዎች እና የ48 የጸጥታ ኃይሎች ሞት መመዝገቡን ገልጿል።

በተጨማሪም ከ10,600 በላይ ሰዎች መታሰራቸውን ድርጅቱ ገልጿል ሲል ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

ኢራን እስካሁን ይፋዊ የሟቾች ቁጥር ያልገለጸች ሲሆን፤ ሮይተርስም የቀረቡትን አሃዞች በተናጥል አጣርቶ ለማረጋገጥ አልቻለም።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢራን ጉዳይ ያሉ አማራጮችን ለመወያየት ማክሰኞ ዕለት ከከፍተኛ አማካሪዎቻቸው ጋር እንደሚገናኙ አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን እሁድ ዕለት ለሮይተርስ ገልጸዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates