ዲፕሎማሲ
የሶማሊያ የፌዴራል መንግሥት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሚንቀሳቀሱ ወታደራዊ እና የጭነት አውሮፕላኖች ወደ አየር ክልሉ እንዳይገቡ መከልከሉ ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 01/05/2018፡- ውሳኔውን የሚያውቁ ምንጮች እንደገለጹት የሶማሊያ መንግሥት ለተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ መንግስት እገዳው በይፋ አሳውቋል።
የሶማሊያ መንግስት ይህም ውሳኔ ላይጨየደረሰው የየመን የደቡባዊ ሽግግር ምክር ቤት መሪ ረቡዕ ዕለት በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ወታደራዊ አውሮፕላን በሞቃዲሾ አድርጎ ኸደ አቡዳቢ መሸሻቸው ተከትሎ ነው።
የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የጭነት አወሮፕላኖች ለሱዳኑ ፈጥኖ ደራሽ ሐይል የጦር መሳሪያ ሲያመላልስም የፑንትላንዱ ቦሳሶ፣ የሶማሊላንዱ በርበራ እና አልፎአልፎም የሶማሊያው ሞቃድሾ የአየር ማረፊያዎች እንደሚጠቁ ሲገለፅ ቆይቷል።



