ዲፕሎማሲ
ቱርኪ በየመን እና ሶማሊያ የተከሰተውን ሁኔታ በንቃት እየተከታተልኩ ነው አለች።

ኢትዮ ሞኒተር፡- 27/04/2018፡- የቱርኪው ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጠይብ ኤርዶጋን ከሳውዲ አረቢያው ልዑል መሀመድ ቢን ሳልማን ጋር በስልክ መወያየታቸው ተገለፀ።
እሁድ እለት ከሳውዲ አረቢያ ልዑል ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት በየመን እና ሶማሊያ የተከሰተውን ሁኔታ “በቅርብ እየተከታተልኩ ነው” ሲሉ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ተናግረዋል።
የሁለቱንም ሀገራት የግዛት አንድነት ለመጠበቅ መረጋጋት አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል።
በስልክ ጥሪው ወቅት ኤርዶጋን እና መሀመድ ቢን ሳልማን በሁለትዮሽ ግንኙነት፣ በቀጠናዊ እና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል ሲል መረጃው አሳይቷል።
ኤርዶጋን በየመን ግጭት ውስጥ ያሉ ወገኖችን ለማሰባሰብ ለሚደረገው ጥረት ቱርኪዬ የበኩሏን ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።
አንካራ በሚቀጥሉት ቀናት ተጨማሪ እርምጃዎችን በመውሰድ በቱርኪዬ እና በሳዑዲ አረቢያ መካከል ያለውን ትብብር ለማሳደግ እንደምትፈልግ ተናግረዋል።
በጋዛ ያለው የሰብአዊ ሁኔታ እየተባባሰ መሆኑን በማስጠንቀቅ ኤርዶጋን ቱርኪዬ በጦርነት በተጎዳው አካባቢ ዘላቂ የሆነ የተኩስ አቁም ስምምነት እና መልሶ ግንባታ እንዲካሄድ መስራቷን ቀጥላለች ብለዋል።



