የተለያዩ
በአፋር ክልል ከባድ ርዕደ መሬት አጋጠመ።

ኢትዮ ሞኒተር፡- 27/04/2018፡- ርዕደ መሬቱ ትናንት ታህሳስ 26 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 5:00 አከባቢ እንዳጋጠመ ቮልካኖ ዲስከቨሪ የተሰኘ ተቋም አስታውቋል።
ይህ በአፋርና በትግራይ የተወሰኑ አከባቢዎች የተሰማው ርዕደ መሬት በሬክተር ስኬል 4.8 የሚለካ እና ከባድ የሚባል መሆኑ ተቋሙ ገልጿል።
የርዕደ መሬቱ ንዝረት በአፋር በራህሌ አከባቢ በከፍተኛ የተሰማ ሲሆን በትግራይ ደግሞ በመቐለ፣ ዓዲግራት፣ ዓዲ ጉደም፣ ማይጨው፣ ውቕሮ፣ ሐይቂ መስሐል፣ ዕዳጋ ሐሙስ፣ ዓድዋ፣ አክሱም እና ሽረ እንዳስላሴ እንደተሰማ የቮልካኖ ዲስከቨሪ መረጃ ያመለክታል።
የርዕደ መሬቱ ንዝረት እንደተሰማቸው የመቐለ፣ ዓድግራትና ማይጨው ነዋሪዎች በማህበራዊ ሚድያ እየገለፁ ይገኛሉ።
ከዚህ በፊት በአፋር ያጋጠመውን ርዕደ መሬት በሰው ህይወት እና ብቤቶች ላይ ጉዳት ማድረሱን የሚታወስ ነው።



