አፍሪካ
በተጠናቀቀው 2025 ዓመት የመጨረሻ ታህሳስ ወር ከተባበሩት ዓረብ ኢሚሬትስ ወደ ሊብያ 59 በረራዎች መደረጋቸው የሳትላይት ምስሎች አሳዩ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 24/04/2018፡- በታህሳስ 2025 ወደ 59 የሚጠጉ የጭነት በረራዎች ወደ ምስራቅ ሊቢያ ሲደርሱ ክትትል ተደርጎባቸዋል፣ ይህም በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ቀጥተኛ መስመሮችን እና የቦሳሶን ጣቢያን በመጠቀም ተከናውኗል ብሏል የወጣው መረጃ።
ከእነዚህ በረራዎች ውስጥ፡ 40ዎቹ በቀጥታ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የተደረጉ ሲሆኑ፣ 19ቱ ደግሞ ከፑንትላንድ እና ሶማሊላንድ ቦሳሶ አየር ማረፊያ ተነስተዋል ይላል።
በሊቢያ ኩፍራህ ውስጥ ወደ 26 በረራዎች መደረጋቸውም ብተመሳሳይ ጠቅሷል።
ኩፍራህ (ሊቢያ) እና ቦሳሶ (ሶማሊላንድ) የሳውዲ አረቢያ ትልቁ የቀይ ባህር ጎረቤት እና ቁልፍ የክልል አጋር የሆነችው ሱዳንን ለማተራመስ አስተዋጽኦ ያደረጉ ሁለቱን በጣም ወሳኝ የሎጂስቲክስ ማዕከላት መሆናቸውም የወጣው መረጃ ያመላክታል።
እነዚህ ሰፈሮች በክልሉ ውስጥ ወታደራዊ እና የፓራሚሊታሪ አቅርቦት ኔትወርኮችን በመጠበቅ ረገድ ማዕከላዊ ሚና ይጫወታሉ።
የሱዳን ጦርነት የውጭ ሐይሎች ጣልቃ ገብነት እንዳለው ሲገለፅ የቆየ ሲሆን በዚህም የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬትስ በዋናነት ትከሰሳለች።
ለፈጣን ድጋፍ ሐይሉ በመደገፍ የምትከሰሰውን ኢሚሬትስ በሊብያ፣ ሶማሊላንድና ፑንትላንድ በኩል ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎች እንደምታስገባ የሳትላይት ምስሎች ያሳያሉ።



