ዲፕሎማሲ

የሶማሊያ ፕሬዝዳንት እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና የሰጠችበት በሦስት ምክንያቶች እንደሆነ ይፋ አደረጉ፡፡

በሌላ በኩል የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ለምን ለሶማሊላንድ እውቅና እንደሰጡ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 23/04/2018፡- ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሐመድ፤ የሶማሊያን የደህንነት መረጃ ጠቅሰው ለአልጀዚራ እንደተናገሩት ሶማሊላንድ ከእስራኤል እውቅና ለማግኘት ሶስት ቅድመ ሁኔታዎችን እንደተስማማች ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሐመድ እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና የሰጠችበት አንዱ ምክንያት እስራኤል ከጋዛ በኃይል የምታፈናቅላቸውን ፍልስጤማውያን ለመቀበል መስማማቷ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ እስራኤል ወታደራዊ ቤዝ እንድታቋቁም ፈቅዳለች ብለዋል። ሦስተኛው ምክንያት ደግሞ የአብርሃም ስምምነት ማዕቀፍ አካል መሆን ነው ብለዋል።

“ፍልስጤማውያንን በግዛቷ ለማስፈር፣ የእስራኤልን የጦር ሰፈሮች በኤደን የባህር ዳርቻ ላይ ለመፍቀድ እና የአብርሃም ስምምነት ማዕቀፍ ሶስቱ የስምምነት አካል ናቸው” ብለዋል ሀሰን ሼክ መሐመድ።

በዚህም መሰረት እስራኤል በአሁን ገጊዜ በሶማሊያ ውስጥ ስራ መጀመሯን እና እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና የሰጠችው በድብቅ እየተካሄደ የነበረውን ግንኙነት ይፋ ለማድረግ ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል።

“እስራኤል ፍልስጤማውያንን በኃይል ወደ ሶማሊላንድ ለማፈናቀል እየሞከረች ነው እናም እስራኤል በሶማሊላንድ የምትሰፍረው ለሰላም አይደለም” በማለት ስምምነቱ ፋርስን እና የኤደን ባሕረ ሰላጤን እንደሚያካትት ገልፀዋል።

“ሶማሊላንድ ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ነፃነትን ስትፈልግ ቆይታለች፣ ነገር ግን በዓለም ላይ እስካሁን እውቅና የሰጣት ሀገር የለም፤ ​​እስካሁን ድረስ ሶማሊላንድን በሰላም አንድ ለማድረግ እየሰራን ቆይተናል” በማለት ከአሁን በኃላ ግን በሐይል የሶማሊያ ግዛት ለማድረግ እንደሚንቀሳቀሱ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡

 

በሌላ በኩል የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ለምን ለሶማሊላንድ እውቅና እንደሰጡ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ ለሱማሊላንድ ለምን እውቅና እንደሰጡ ሲናገሩ ‘’ሶማሊላንድ ሙስሊም አገር ናት፡፡ ስድስት ሚሊዮን የተረጋጉ ሙስሊሞች የሚኖሩባትና የአብርሀምን ስምምነት መቀላቀል የሚፈልጉ ህዝቦች ያሉባትም ናት’’ ያሉት ሲሆን ይህም በራሱ ጥሩ ነገር መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ኔታኒያሁ ጨምረውም ‘’ሶማሊላንዶች ዲሞክራቶች ናቸው፣ ምርጫ ያደርጋሉ፡፡ የተቀረው ሶማሊያ ግን በአልሸብብ ከባድ ትርምስ ውስጥ የገባ ከመሆኑም በላይ ከአስር አመት በላይ ምርጫ አድርጎ አያውቅም፡፡ ስለዚህም ከሱማሊያ ይልቅ ሱማሊላንድ የተረጋጋ አገር ነው’’ ብለዋል፡፡

‘’እንደዚህ አይነት የተረጋጋና ዲሞክራሲያዊ አገር የአብርሀም ስምምነትን ለመፈረም ፈቃደኛ ሲሆን ማንም ሰው እምቢ አይለውም፡፡ የወሰድነው እርምጃ ሁሉም የሚያደርገውን ነው‘’ በማለት ገልፀዋል፡፡

ኔታኒያሁ ሁሉም አገር ለሱማሊላንድ እውቅና ለመስጠት ጫፍ ላይ መድረሱን ጠቅሰው ‘’ነገር ግን የአጋጣሚ ሆኖ እኛ የመጀመሪያ ሆነናል‘’ በማለትም ተናግረዋል፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates