በየሳምንቱ በአማካይ 850 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች የየመንን ድንበር አቋርጠው ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመግባት እንደሞሞክሩ አንድ ሪፖርት አመለከተ።
በሌላ ዜና ሰሙኑን ከሊቢያ ወደ ጣሊያን ለመሻገር የሞኮሩር 117 የአፍሪካ ስደተኞች በባህር መስመጣቸው ታውቀዋል፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 22/04/2018፡- የዓለም አቀፉ ስደተኞች ድርጅት ሪፖርት እንደሚያሳየው በጥቅምት ወር 2018 የየመንን ድንበር ከተሻገሩት ውስጥ 14,126ቱ ወደ ሳዑዲ አረቢያ እያመሩ ነበር።
በጥቅምት ወር 2018 ዓ/ም የወጣው የተመድ የስደተኞች ድርጅት ሪፖርት መሠረት በየወሩ 45,150 ዜጎች ድንበሩን ያቋርጣሉ።
ከእነዚህ ስደተኞች መካከል አብዛኞቹ ኢትዮጵያዊያን እንደሆኑ የሚገልፀው ሪፖርቱ የስደተኞቹ ቁጥር ከጊዜ እየጨመረ መምጣቱን አስታውቀዋል፡፡
በሌላ ዜና በዚህ ሳምንት ከሊቢያ ወደ ጣሊያን ለመሻገር 117 የአፍሪካ ስደተኞች ጭና ስትጓዝ የበረችው ጀልባ በመስመጥዋ 116ቱ መሞታቸው ታውቀዋል፡፡
ጀልባው በባህሩ ማኸል ሲትደርስ ባጋጠመው ከፍተኛ ማዕበል እንደተገለበጠች የሚናገሩት የአይን እማኞች ከ117ቱ ተጓዦች አንድ ሰው በተአምር በህይወት መትረፉን ገልፀዋል፡፡ ይህም የስደት አስከፊነት ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ክስተት ነው ተብለዋል፡፡
በሌላ በኩል ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት የተጠናቀቀውን የ2015 ዓመት እና አዲሱ የ2026 የሰብአዊ እርዳታ ሪፖርት ያወጣ ሲሆን በ2026 በዓለም ዙሪያ 239 ሚሊዮን ሰዎች የሰብአዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ብለዋል።
2025 ግጭቶች የበዙበት እና ሰብአዊ እርዳታን ለማድረስ አስቸጋሩ የሆነበት ዓመት እንደነበር በመጥቀስ አዲሱ ዓመትም በርካታ ሰዎች ለሰብአዊ እርዳታ እጃቸው የሚዘረጉበት ዓመት እንደሚሆን አስታውቀዋል፡፡



