ኢኮኖሚ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የ7 በመቶ ዝቅተኛ የቁጠባ ወለድ ማንሳቱን አስታወቀ፡፡

ባንኮች በየራሳቸው የወለድ መጠን እንዲተምኑም ፈቅደዋል፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 22/04/2018፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለዘመናት ተግባራዊ ሲያደርግ የቆየውንና በሕግ ተወስኖ የነበረውን የ7 በመቶ ዝቅተኛ የቁጠባ ወለድ በማንሳት፣ ከዚህ በኋላ የወለድ መጠን በገበያ ፍላጎትና አቅርቦት እንዲወሰን መወሰኑን አስታወቀ።

ባንኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስላለፈው ይህ ታሪካዊ ውሳኔ፣ ከሐምሌ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ ያለውን በወለድ ላይ የተመሰረተ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ያለመ ነው።

እንደ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፓሊሲ ኮሚቴ መረጃ ከሆነ፤ ቀደም ሲል መንግስት ዝቅተኛውን የወለድ መጠን ወስኖ አስቀማጮች በከፍተኛው መጠን ላይ ብቻ እንዲደራደሩ የሚያደርገው አሰራር ተቀይሮ፣ አሁን ግን የወለድ ተመኑ በአስቀማጮች እና በባንኮች መካከል በሚደረግ ነፃ ድርድርና ስምምነት እንዲወሰን በባንኩ ቦርድ ጸድቋል።

የዚህ ፖሊሲ ዋና ዓላማ በኢኮኖሚው ውስጥ የሚዘዋወረውን የገንዘብ መጠን በወለድ በኩል በመቆጣጠር የዋጋ ንረትን ለማረጋጋትና የባንኮችን የውድድር መንፈስ በማሳደግ ቁጠባን ለማበረታታት መሆኑ ተጠቁሟል።

ብሔራዊ ባንክ አክሎም፣ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲው በዋጋ መረጋጋት ላይ ችግር እንደሚገጥመው በተረዳ ጊዜ ያሉትን የፖሊሲ መሣሪያዎች ሁሉ እንደሚጠቀም አስታውቋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates