ኢትዮጵያ

የባሕር በር ጥያቄ አሁን ላይ ጥያቄው እንዴት ይመለስ? ወደሚለው ተግባራዊ ምዕራፍ መሸጋገሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ገለፁ፡፡

የባሕር በር ጥያቄ የውስጥ ልዩነቶችን የሚሻገር የትውልድ ጥያቄ ሆኖዋል ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 21/04/2018፡- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው የ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ፣ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ከምክር ቤት አባላቱ ለሚኒስትሩ ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል፤ ኢትዮጵያ በታሪካዊ ስህተትና ግፍ የተነፈገችውን የባሕር በር ለማስመለስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምን እየሠራ እንደሆነና ከዜጎች ምን እንደሚጠበቅ ተነስተዋል፡፡

ሚኒስትሩ ለቀረበው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፤ የባሕር በር ጥያቄው ምላሽ እንዲያገኝ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በሚያስከብር መልኩ በስፋት እየተሠራበት መሆኑን ገልጸዋል።

እስካሁንም የኢትዮጵያ ጥያቄ እና የፍላጎቷ ምንነት ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ በግልጽ ማስረዳት መቻሉን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያን ፍላጎት የማስገንዘቡ ሥራ ውጤት ማስገኘቱን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፤ አሁን ላይ ጥያቄው እንዴት ይመለስ? ወደሚለው ተግባራዊ ምዕራፍ መሸጋገሩን አብራርተዋል።

የባሕር በር የአንድ ፓርቲና ወገን ወይም የግለሰብ ጥያቄ ሳይሆን የሀገርን ዘላቂ ጥቅም የሚያረጋግጥና የውስጥ ልዩነቶችን የሚሻገር የትውልድ ጥያቄ በመሆኑ፤ ጥያቄው ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ ሁሉም ዜጋ ያለልዩነት በአንድነት ሊቆም እንደሚገባ አሳስበዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates