ፖለቲካ

እስራኤል በሉኣላዊነትዋ ወታደራዊ ቤዝ እንድታቋቁምና ሌላ ሀገርን እንድትወጋ እንደማትፈቅድ ሶማሊያ አስታወቀች፡፡

ለሶማሊላንድ የሰጠችው የሀገርነት እውቅናም ሉአላዊነትዋ መደፈር አደርጋ እንደምትመለከተው ገልፃለች፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 20/04/2018፡- እስራኤል ለሶማሊላንድ የአገርነት እውቅና የሰጠች የመጀመሪያ ሀገር መሆንዋ ተከትሎ በርካታ ተቃውሞ እየገጠማት ስሆን የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ካቢኒያቸውን ሰብስቦ ውሳኔ አሳልፈዋል፡፡

የእስራኤልን ውሳኔ ያወገዘው ካቢኔው ሶማሊያ ብምንም ተአምር ሉአላዊነትዋ አሳልፋ እንደማትሰጥ እና ሶማሊላንድ አንድ አካል ሶማሊያ መሆንዋ በጠንካራ አቋም አስተዋውቀዋል፡፡

የሶማሊው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ የእስራኤል ውሳኔ ሽበርተኞችን እንዲስፋፉ እና ቀጠናውን ለመተራመስ ዕድል ከመፍጠር ውጪ ሶማሊላንድን የሶማሊያ የግዛት አከል ከመሆን እንደማያድናት ገልፀዋል፡፡

ውሳኔውን ለመቀልበስም የተቻለውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡

የእስራኤል ውሳኔ ተከትሎ ሶማሊያዊያን በሞቃድሾ ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ ያሰሙ ሲሆን የፍስጤምን ባንዴራ ሲያውለበልቡ ተስተውልዋል፡፡

በአንፃሩ ሶማሊላዳዊያን በሃርጌሳ እና ሌሎች ከተሞች የደስታ ሰልፍ ባደረጉበት ወቅት የእስራኤል ባንዴራ በማንጠፍ አምላካቸው ሲያመሰጉንበት ታይተዋል፡፡

የእስራኤልን ውሳኔ የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ በርካታ አገሮች የተቃወሙት ሲሆን ከእስራኤል ቀጥሎ እስካሁን የሀገርነት እውቅናውን ያረጋገጠ ሌላ አገር የለም፡፡

በተጨማሪም እንደ ባሕረ ሰላጤው የትብብር ምክር ቤት፣ የእስልምና ትብብር ድርጅት፣ የአፍሪካ ሕብረት እና የአውሮፓ ሕብረት ያሉ ዋና ዋና ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት በእስራኤል አካሄድ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ገልጸዋል።

የፀጥታው ምክር ቤት እስራኤል ለሶማሊላንድ በሰጠችው እውቅና ላይ ለመወያየት ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ የጠራ ሲሆን አንዳንድ ተንታኞች በውሳኔው ተቃውሞ ይሰጣል እያሉ ይገኛሉ፡፡

አንዳንድ የመካከለኛ መስራቅ የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና የሰጠችበት ምክንያት በበርበራ ወታደራዊ ቤዝ በማቋቋም የየመን ሄቲዎችን ለመምታት በማለም ነው፤ የመጀመሪያውና የመጨረሻው ዓላማዋ እሱ እና እሱ ብቻ ነው፡፡

ሁቲ የእስራኤል በሶማሊላድ መኖር እኛ ላይ የተቃጣ ዒላማ አድርገን እንመለከተዋለን ብለዋል፡፡

የቡድኑ መሪመሪ አብደል-ማሊክ አል-ሁቲ « በሶማሊያ ውስጥ የእስራኤል መኖር ለጦር ሰራዊታችን ወታደራዊ ኢላማ እንደሆነ እንቆጥረዋለን፤ በሶማሊያ እና በየመን ላይ የሚሰነዘር ጥቃትም ለክልሉ ደህንነት ስጋት ነው» ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

የሁቲ  መሪው  እርምጃው አስከፊ መዘዝ እንደሚያስከትል አስጠንቅቀው፣ ለሶማሊላድ እውቅና መስጠት “ሶማሊያንና የአፍሪካ አካባቢን እንዲሁም የመን፣ ቀይ ባህርን እና በሁለቱም የቀይ ባህር ዳርቻዎች ላይ ያሉት አገራት  ያነጣጠረ ነው” ብለዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates