ኢኮኖሚ

ግብፅ ከጅቡቲ ጋር የገባቸውን ውል መጨረስዋ ተሰማ፡፡

ሁለቱ አገራት በ3 ጉዳይ ላይ ስምምነት ማድረጋቸው ታውቀዋል።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 20/04/2018፡- ወደ ጅቡቲ ያመሩት የግብፅ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሌ/ጀነራል ከማል ኤል ዋዚር  የወደብ ልማት ስምምነት የተባለለትን ስምምነት ከጅቡቲ ተፈራርመዋል።

ከስምምነቱ መካከል የግብፁ ኤልስዌዴ ኤሌክትሪክ በዶራሌ የኮንቴነር ወደብ 23 ሜጋ ዋት የሚያመነጭ የፀሃይ ሃይል መሰረተልማት መገንባት የሚያስችል ነው የተባለ ሲሆን እንዲሁም የግብፅ ጭነቶችን ማስተናገጃ 10 ሄክታር መሬት በጅቡቲ አለምአቀፍ ነፃ ንግድ ቀጠና መስጠትን ያካትታል።

በተጨማሪ በጅቡቲ ግሬት ሆርን ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና በግብፁ የመንግስት ኩባንያ ሆልዲንግ ካምፓኒ ፎር ማሪታይም እና የብስ ትራንስፖርት መካከል የተደረ የመግባቢያ ሰነድ ስምምነትም የተካተተበት ነው።

በስምምነቱ መሰረት 5 ሚሊየን ኮንቴነር ማስተናገድ የሚችል አዲስ የኮንቴነር ወደብ ለመገንባት በመርህ ደረጃ ስምምነት ተደርሷል።

የት አካባቢ እና መቼ ወደቡ ይገነባል የሚለው ግን አልተገለፀም።

የግብፅ መንግስት የአሰብ ወደብ ለማልማትም ከኤርትራ መንግስት ጋር መስማማቱ የተገለፀ ሲሆን እንደ ጅቡቲው ግን ይፋዊ ስምምነት ሲፈፅም አልታየም፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates