ኤስያ

እስራኤል ለሶማሊላንድ የሀገርነት እውቅና መስጠትዋ ተከትሎ ቻይና ወደ ታይዋን ሰራዊትዋ ማስጠጋትዋ ተሰማ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 20/04/2018፡- ቻይና የታይዋንን ዋና ዋና ወደቦች የመዝጋት ሙከራን የሚያካትት እና “ለወራሪዎች እና ለውጭ ኃይሎች ጥብቅ ማስጠንቀቂያ” ነው ያለችውን ከፍተኛ ወታደራዊ ልምምድ በታይዋን ዙሪያ ማድረግ መጀመርዋ እየተገለፀ ይገኛል።

ዛሬ ሰኞ የተጀመረው ይህ የቀጥታ ተኩስ ልምምድ፣ የአየር ኃይል፣ የባህር ኃይል እና የሮኬት ወታደሮችን ያሳተፈ ሲሆን፣ የታይዋን መከላከያ ኃይል የአጸፋ መልስ ለመስጠት ወታደሮቹን እና የጦር መሳሪያዎቹን በተጠንቀቅ ማሰማራቱን ተሰምተዋል።

ይህ የቤጂንግ እርምጃ የመጣው አሜሪካ ለታይዋን የ11.1 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ ሽያጭ ማጽደቋን እና የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሳናይ ታካይቺ ቻይና በታይዋን ላይ ጥቃት ከሰነዘረች የጃፓን ጦር ጣልቃ ሊገባ እንደሚችል ፍንጭ መስጠታቸውን ተከትሎ ነው።

ቤጂንግ ታይዋንን የራሷ ግዛት አካል አድርጋ የምትቆጥር ሲሆን አስፈላጊ ከሆነም በኃይል እንደምትቆጣጠራት ስትገልጽ ቆይታለች።

የቻይና ጦር እንደገለጸው፣ በታይዋን ሰሜን እና ደቡብ ምዕራብ አቅጣጫዎች  የምድር እና የባህር ኢላማዎች ልምምድ አድርገዋል።

“Just Mission 2025” ተብሎ የተሰየመው ይህ ልምምድ ማክሰኞም የሚቀጥል ሲሆን፣ የደሴቷን ቁልፍ ወደቦች የመዝጋት እና ደሴቷን የመክበብ እንቅስቃሴዎችን እንደሚያደርግ ይገመታል።

የታይዋን ፕሬዝዳንቱ ጽህፈት፣ ቻይና ዓለም አቀፍ ህጎችን በመጣስ እያደረገች ያለውን ወታደራዊ ማስፈራራት በማውገዝ ፣ ቤጂንግ ይህንን “ኃላፊነት የጎደለው ትንኮሳ” በአስቸኳይ እንድታቆም ጠይቀዋል።

የታይዋን መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ሁለት የቻይና የጦር አውሮፕላኖች እና 11 መርከቦች በደሴቷ ዙሪያ ሲንቀሳቀሱ መታየታቸውን ገልጾ፣ የታይዋን ጦር በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኝ እና “ፈጣን የአጸፋ ምላሽ” ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።

ቻይና ይህን አዲስ እንቅስቃሴ የጀመረችው እስራኤል ለሶማሊላንድ የአገርነት እውቅና መስጠትዋ ተከትሎ ታይዋንም ተመሳሳይ ዕድል ታገኛለች በሚል ስጋት መሆኑ እየተገለፀ ነው፡፡

ቻይና የእስራኤለ ውሳኔን በመቃወም የሶማሊያ ሉአላዊነትና አንድነት እንደምትደግፍ አስታውቃለች፡፡

Show More

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates