አፍሪካ

የሱዳን ሰራዊት የጦር መሣሪያዎች በጫኑት የፈጥኖ ደራሽ ሐይሉ ኮንቮዮች ላይ ጥቃት መፈፀሙ ተገለፀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 15/04/2018፡- ከአል ኩፍራህ አየር ማረፊያ የጦር መሳሪያዎችን ይዘው ወደ ሱዳን በሚጓዙ የፈጥኖ ደራሽ ሐይሉ ኮንቮዮች ላይ የአየር ድብደባ ተካሂዷል ሲል አሶሼትድ ፕረስ ዘግበዋል።

ጥቃቱ ከሊቢያ የሚመጣውን የRSF የአቅርቦት መስመሮችን እና የሎጂስቲክስ አውታረ መረብን ለማፍረስ የታሰቡ እና እነዚህ ጥቃቶች በሊቢያው ፊልድ ማርሻል ሃፍታር ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ ተገልፀዋል፡፡

ይህም በሦስት ድንበር አካባቢ ወደ ሱዳን የሚደረገው ማንኛውም የRSF እንቅስቃሴ ከእንግዲህ እንደማይታገስ ግልጽ ለማድረግ ነው ብለዋል የሱዳን ጦር።

የሱዳን የጦር ኃይሎች እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ይህንን ስትራቴጂ ለምን አላቆሙም ነበር በማለት በርካቶች እየጠየቁ ይገኛሉ፡፡

የአል ኩፍራህ አየር ማረፊያ በፊልድ ማርሻል ሃፍታር ቁጥጥር ስር ባለው የሊቢያ ብሔራዊ ጦር ግዛት ውስጥ ለፈጣን የድጋፍ ኃይሎች ዋና የሎጂስቲክስ ማዕከል ሆኖ እያገለገለ እንደሚገኝ መረጃዎች ያሳያሉ።

አየር ማረፊያው የፈጣን ድጋፍ ሐይሉ የጦር መሳሪያዎችን እና ቅጥረኞችን ይዘው በደርዘን የሚቆጠሩ የውጭ የትራንስፖርት አውሮፕላኖች እዚያ ሲያርፉ በሳትላይት ታይተዋል።

ታጣቂ ቡድኑ የሶስት ድንበር ዞን አቋርጦ ወደ ደቡብ የትራንስፖርት የጭነት መኪናዎችን ወደ ሱዳን ይልካል፣ ከዚያም ወደ ዳርፉር ወደሚገኘው የRSF ምሽግ ይጓዛሉ [በቅርብ ሳምንታት በRSF ኮንቮዮች ላይ የተሰነዘሩት ሁሉም የአየር ጥቃቶች ይህንን መንገድ ተጠቅሞ ነው ይላል መረጃው፡፡

በአል ኩፍራህ በኩል የሚደረገው የመልሶ አቅርቦት ጥረቶች የጀመሩት የሱዳን ጦር ኃይሎች ካርቱምን ከተቆጣጠረ በኃላ እንደሆነ ተገልፀዋል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates