ኢኮኖሚ

ቱርክ በሶማሊያን የዓሳ ማጥመድ ስራ ለመስራት የሚያስችላት ስምምነት መፈጸምዋ ተገለፀ፡፡

ቱርክ ከዚህ በፊት ጋዝና ነዳጅ ለማውጣት ስምምነት መፈፀምዋ ይታወሳል፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 08/04/2018፡- ቱርክ ትርፋማ የሆነው የነዳጅ እና የጋዝ ስምምነት ካገኘች በኋላ አሁን ደግሞ የዓሣ ማጥመጃ ዘርፉን ለመቆጣጠር ትኩረቷን አዙራለች ይላል መረጃው።

በዚህ ሳምንት ቱርክ ከሶማሊያ ጋር “ለሶማሊያዎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል” የተባለለት የዓሣ ማጥመጃ ስምምነት ተፈራረመች።
ስምምነቱ የፈፀመው ደግሞ የቱርክ ጦር የኢንቨስትመንት/የንግድ ኩባንያ የሆነው ኦያክ እንደሆነ ተገልፀዋል፡፡

ኦያክ፣ የቱርክ የጦር ኃይሎች ድጋፍ እና የጡረታ ፈንድ በመባል የሚታወቀው ሲሆን፣ የቱርክ ትልቁ የሙያ ጡረታ ፈንድ ነው። በ1961 በሕግ የተቋቋመው ኦያክ፣ ከብሔራዊ የማህበራዊ ዋስትና ስርዓት ነፃ ለሆኑ የቱርክ ጦር ኃይሎች አባል መኮንኖች፣ ኮሚሽን የሌላቸውን መኮንኖችን እና የተወሰኑ የሲቪል ሠራተኞችን ጨምሮ ተጨማሪ የጡረታ፣ የአካል ጉዳት እና የሞት ጥቅማ ጥቅሞችን የሚሰጥ ነው።

ወደ 470,000 የሚጠጉ አባላት ያሉት ድርጅቱ በቱርክ የሲቪል እና የንግድ ሕግ መሠረት እንደ የግል አካል ሆኖ ይሠራል ተብለዋል።
ከቱርክ ትልቁ የኢንዱስትሪ ኮንግሎሜሬትስ አንዱ እንደሆነ የሚነገርለት ኦያክ፣ ከ130 በላይ ኩባንያዎች ከስሩ ያሉት እና ከ38,000 በላይ ሰዎችን ቀጥሮ የሚሰራ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ።

ይህ ድርጅት አሁን እግሩ ሶማሊያ ምድር ላይ ረግጠዋል፡፡ በሶማሊያ የሚገኘውን የዓሳ ሃብት ብማውጣት ለውጭ ለመላክ ማቀዱን ተገልፀዋል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates