አፍሪካ

የአይ ኤስ አይ ኤስ መሪ በቦሳሶ በሚገኘው ሆስፒታል ውስጥ የህክምና አገልግሎት ሲያገኝ ነበር መባሉ በፑንትላንድ ትልቅ ውዝግብ ፈጠረ ተባለ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 05/04/2018፡-  የአይ ኤስ አይ ኤስ የበላይ መሪ የሆነው አብዲቃዲር ሙሚን በቦሳሶ በሚገኝ ሆስፒታል መታከማቸውን ዓለም አቀፍ ሚድያዎች ከዘገቡ በኋላ ፑንትላንድ ትልቅ ቅሌት እያጋጠማት ነው ተብለዋል።

የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ሙሚን በግል ባለቤትነት በተያዘ ሆስፒታል በድብቅ መታከሙን ያሳያል፣ ይህም ስለ ፑንትላንድ የደህንነት እና አስተዳደር ጉዳይ ከባድ ጥያቄዎችን አስነስቷል።

ይህ ክስተት ፑንትላንድ ቀደም ሲል ሙሚን ለረጅም ጊዜ ተደብቆ በነበረበት ካልሚስካድ ተራሮች ውስጥ ባደረገችው ኦፕሬሽን መሪውን ጨምሮ በርካቶች እንደደመሰሰች የተናገረችውን አባባል በቀጥታ እንደሚቃረንም እየተገለፀ ነው።

ፑንትላንድ ያደረገችው ኦፕሬሽን ስኬታማ እንደነበር ብታስታውቅም የቡድኑ መሪ በቦሳሶ የህክምና ማእከል በነፃ አገልግሎት አገኘ መባሉ ግን ከባድ የደህንነት ውድቀት እና የውስጥ ሙስናን ያሳያል ተብለዋል።

በቅርብ ጊዜ የወጡ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት ሙሚን በአሁኑ ጊዜ በካልሚስካድ ተራሮች ውስጥ ይገኛል፣ ይህም የፑንትላንድ ጥቃቶች ውጤት እንዳላሳኩ የበለጠ ያረጋግጣሉ።

የሶማሊያ የፌዴራል መንግስት እና ዓለም አቀፍ አጋሮች አሁን የሙሚንን የህክምና አገልግሎት ማን እንዳመቻቸ እና ወደ ከተማው እንዴት መድረስ እንደቻለ ለማወቅ መደበኛ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

ይህ ክስተት ፑንትላንድ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ካጋጠማት ትልቁ የጸጥታ ቅሌት ሆኗ የተመዘገበ ሲሆን፣ ህዝቡም ሆነ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከአስተዳደሩ ግልጽነት፣ ተጠያቂነት እና ትክክለኛ ማብራሪያ እንዲሰጥ እየጠየቁ ይገኛሉ።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates