አፍሪካ

የኤርትራ መንግስት ለበርካታ አመታት በእስር ያቆያቸውን 98 ዜጎቹን መልቀቁን ተሰማ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 05/04/2018፡- የተለያዩ የመረጃ ምንጮች እንደገለፁት በኤርትራ መንግስት ለአመታት ታስረው የቆዩ 98 ሰዎች ሰሞኑን ተለቀዋል፡፡

እስከ አምስት አመት የሚደርስ ጊዜ በእስር የቖዩት እነዚህ ሰዎች በሙሉ ከሀይማኖት ጋር በተያያዘ የታሰሩ ናቸው፡፡

እንደምንጮቹ ከሆነ ባሳለፍነው ሳምንት ሀሙስ እለት 36 ሰዎች ከእስር የወጡ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 20 ያህሉ ሴቶች ናቸው፡፡
በተጨማሪም ትላንት ደግሞ ሌሎች 17 ሰዎች ተፈተዋል፡፡

ከአንድ ሳምንት በፊት በተመሳሳይ 29 ሰዎችና 19 ሰዎች በተለያየ ጊዜ መለቀቃቸውን የገለፁት ምንጮቹ በያዝነው ወር በጠቅላላው 98 እስረኞች በዋስ መፈታታቸውን አስረድተዋል፡፡

የሰብአዊ መብት ተቋማት እንደሚናገሩት በኤርትራ በ2002 በወጣው ህግ በመሰረት ከኦርቶዶክ፣ ተዋህዶ፣ ሉተራን፣ ካቶሊክና ሱኒ ሙስሊም ሀይማኖቶች በስተቀር ሌሎች ሀይማኖቶችን መከተል በይፋ ተከልክሏል፡፡

በእስር ላይ የቆዩት እነዚህ ሰዎች ከተጠቀሱት ሀይማኖቶች ውጭ የሚከተሉ ሲሆን በርካታ ተከታይ እንዳላቸውም ይነገራል፡፡

እነዚህ 98 እስረኞች የተፈቱ ቢሆንም ማይ ስርዋ በተሰኘው እስር ቤት በተመሳሳይ የታሰሩ ሌሎ በርካቶች እንዳሉ መረጃዎቹ አስረድተዋል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates