የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በ2026 የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊነት ጥረቶችን ለመደገፍ የ550 ሚሊዮን ዶላር ቃል መግባቷ አስታወቀች።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 203/04/2018፡- የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን በሰጡት መመሪያ መሠረት አገሪቱ ለ2026 የተባበሩት መንግስታት አለም አቀፍ የሰብአዊነት አጠቃላይ እይታ (GHO) ለመደገፍ አዲስ 550 ሚሊዮን ዶላር ቃል መግባቷን አስታውቃለች።
ይህ ድጋፍ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በዓለም ዙሪያ በሚገኙ 23 የሰብአዊነት ስራዎች ውስጥ በግምት 135 ሚሊዮን ሰዎችን ለመርዳት 33 ቢሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ ያቀደውን እቅድ ይደግፋል ተብሏል።
ድጋፉ ቅድሚያ አስቸኳይ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው 87 ሚሊዮን ሰዎች ሲሆን ይህም 23 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቅ ነው።
ይህ ተነሳሽነት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ቀጣይነት ባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ተሳትፎ ላይ የተመሰረተ መሆኑን የገለፀው የኢሚሬትስ መንግስት በዚህም ከዚህ ቀደም ከ375 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ እርዳታ በማቅረብ በዓለም ዙሪያ ከአንድ ቢሊዮን በላይ ሰዎችን መድረሱን አስታውቋል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በችግር ጊዜ ምላሽ ውስጥ ግንባር ቀደም አስተዋፅዖ አበርክቷል ያለ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ፡ለጋዛ ከ40% በላይ የሚሆነውን ዓለም አቀፍ እርዳታ የሚይዝ 2.65 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሰብአዊ እርዳታ፣ እንዲሁም ከ100,000 ቶን በላይ የእርዳታ አቅርቦቶችን፤ ለሱዳን ከጦርነቱ በኃላ 784 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ፣ ከ2015-2025 ደግሞ በአጠቃላይ 4.24 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ አርጋለሁ ብሏል።
በዩክሬን ለሰብአዊ ድጋፎች 105 ሚሊዮን ዶላር፣ በአፍሪካ ውስጥ ባለፉት አስርት ዓመታት በድምሩ ወደ 21 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚጠጋ የልማት እና የሰብአዊ እርዳታ መድረጉም ጨምሮ አስታውቋል።



