አፍሪካ

የአፍሪካ ሕብረት በሱዳን ኮርዶፋን ግዛት የተፈፀመውን አሰቃቂ ጥቃት አወገዘ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 20/03/2018፡- የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበርም በፈጣን ድጋፍ ሐይሉ የሚደገፉ ሚሊሻዎች (ጃንጃዊድ) በንፁሃን ዜጎች የፈፀሙት ጥቃት ብፁኑ አውግዟል።

በደቡብ ኮርዶፋን በሲቪሎች ላይ የሚፈጸሙ አስከፊ ወንጀሎች ሲቀጥሉ፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ማሃሙድ አሊ ዩሱፍ ፈጣን ድጋፍ ሚሊሻ (ጃንጃዊድ) በካሎጊ የፈጸሙትን ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት የሚያወግዝ ጠንካራ መግለጫ አውጥተዋል።

ጥቃቱ ከመቶ በላይ የሚሆኑ ሲቪሎችን፣ በመዋዕለ ሕፃናት ውስጥ በደርዘን የሚቆጠሩ ሕፃናትን ጨምሮ፣ እንዲሁም የቆሰሉ ሰዎችን ለማዳን ሲሞክሩ ኢላማ የተደረጉ አስተማሪዎችን እና ሐኪሞች ተገድሏል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ክቡር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ በደቡብ ኮርዶፋን ካሎጊ በህጻናት፣ አስተማሪዎች፣ የህክምና ባለሙያዎች እና ሲቪሎች ሆን ተብሎ ኢላማ ማድረግ የዓለም አቀፍ የሰብአዊነት እና የሰብአዊ መብቶች ህግን በግልጽ ተጥሷል ብሏል።

ደም መፋሰሱን ለማስቆም ሁሉም ወገኖች አስቸኳይ እና ያለ ቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እንዲሁም የሲቪሎችን – በተለይም ህጻናትን፣ ሴቶችን እና አረጋውያንን – ከዓለም አቀፍ ሕግ ጋር በሚስማማ መልኩ ሙሉ ጥበቃ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ይህ በእንዲህ እያለ ግብፅ አንዲት ሱዳን እንድትኖር እሰራለሁ አለች።

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደል አቲ ትላንት ከአልጃዚራ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ግብፅ በሱዳን ቀውስ ያላትን ጠንካራ አቋም ደግሞ አረጋግጠዋል።

ግብፅ ሱዳንን በማንኛውም ምክንያት ለመከፋፈል የሚደረግ ማንኛውንም ሙከራ እንደማትቀበል እና የሱዳን አንድነት እና የግዛት አንድነት መጠበቅ እንዳለበት ተናግረዋል።

አብደል አቲ የሱዳንን ህዝብ ሀብት መጠበቅ አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተው፣ ይህንንም የሱዳንን ብሔራዊ ተቋማት ከመጠበቅ ጋር የተያያዘ ወሳኝ ኃላፊነት እንደሆነ ገልጸውታል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates