መካከለኛ ምስራቅ

ሳውዲ ዓረብ ከፍተኛ ጦር ወደ የመን ማስገባቷ ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 20/03/2018፡- ቪዲዮዎች እንደሚያሳዩት ትላልቅ የሳውዲ ወታደሮች በአል-ዋዲያ በኩል ወደ የመን የገቡ ሲሆን፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከሚደገፉት የSTC ሚሊሻዎች ጋር በተፈጠረው ውጥረት ምክንያት እንደሆነ እየተገለፀ ነው።

የሳውዲ አረቢያ በታንኮች የታጀበ የጦር እንቅስቃሴ በየመን ያለውን ውጥረት እንዳያባብሰው ተሰግቷል።

በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሚደገፉ የSTC ኃይሎች በምስራቅ በተለይም ከኦማን ድንበር ላይ በሚገኘው ማህራ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ያደረጉት በከፍተኛ እንቅስቃሴ ሳውዲ ወታደሮቿ ወደ የመን እንድታስገባ እንዳስገደዳት እየተገለፀ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በሳውዲ የሚደገፉት የብሔራዊ ጋሻ ኃይሎች በቅርቡ በአል-ማህራ ከያዙት በርካታ ቁልፍ ቦታዎች ማለዳ ላይ መልቀቃቸው ተገልጿል።

በየመን የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬትስ እና ሳውዲ ዓረቢያ የሚደገፉ ሁለት ቡድኖች እየተፋለሙ የሚገኙ ሲሆን አሁን የሳውዲ ጦር መግባቱ ሁኔታውን ያባብሷል እየተባለ ነው።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates