ዲፕሎማሲ

በሱማሊያ ያለውን ችግር ለመቅረፍ አለም አቀፍ ቅንጅት እንደሚያስፈልግ ግብፅ አስታወቀች፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 20/03/2018፡- ሱማሊያ እንዳንገባ የበጀት እጥረት እንቅፋት ሆኖብናል›› ሲሉ የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ፡፡

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በድር አብደል አቲ በኳታር እየተከናወነ ባለው ዶሀ ፎረም ላይ ባደረጉት ንግግር በሱማሊያ ያለውን ችግር ለመቅረፍ አለም አቀፍ ቅንጅት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል፡፡

በንግግራቸው ”አንዳንድ አካላት ቀጣናውን የፉክክር ሜዳ ለማድረግ ጥረት እያደረጉ ነው” ያሉት ሚኒስትሩ ጨምረውም እንደዚህ አይነቱ አካሄድ ለሱማሊያ የግዛት አንድነትና በቀይ ባህር አካባቢ ላለው መረጋጋት ስጋ እየፈጠረ መምጣቱን አስታውቀዋል፡፡

”ሱማሊያ ለግብፅ፣ ለአረብና ለአፍሪካ ብሄራዊ ደህንነት ቁልፍ ናት” በማለት የገለፁት ሚኒስትሩ አገራቸው በሱማሊያ ላይ ያላት ፖሊሲ የግዛት አንድነቷን የሚያረጋግጥ እንደሆነና ማንኛውንም አይነት ይህንን የሚፃረር የተናጥል እርምጃ የማይቀበል መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

አገራቸው የሱማሊያን መንግስት አቅም ለመገንባት የሚያስችሉ የተለያዩ ድጋፎችን ስትሰጥ መቆየቷንና በዚህም እንደምትቀጥልበትም አስረድተዋል፡፡

በድር አብደል አቲ ሲቀጥሉም ”ለሱማሊያ መረጋጋት ወሳኝ የሆነውን የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ሀይል(ኤዩሶም) ያለንን ድጋፍ እንገልፃለን፡፡ በድጋፋችንም እንቀጥላለን” ብለዋል፡፡

በሰላም አስከባሪው ሀይል ውስጥ ግብፅ ወታደሮቿን ለመጀመሪያ ጊዜ በሱማሊያ ለማሰማራት ፈቃደኝነቷን ማሳየቷን ያስታወቁት ሚኒስትሩ ይሁንና የበጀት እጥረት እንቅፋት እንደፈጠረባቸው ገልፀዋል፡፡

ከቀድሞው ሰላም አስከባሪ ሀይል ወደአዲሱ ኤዩሶም በሚደረገው ሽግግር ላይ የበጀት እጥረት ማጋጠሙ የሱማሊያን መረጋጋት ስጋት ውስጥ እንደከተተው ጠቅሰውም አለም አቀፉ ማህበረሰብና አጋሮች በአስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates