የአየር ንብረት አካባቢ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሐፊ ጋር ተወያዩ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 25/03/2018፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሐፊ ክላቨር ጋቴቴ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መረጃ÷ “ከተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሐፊ ክላቨር ጋቴቴ ጋር እ.ኤ.አ በ2027 አፍሪካን በሚገባ የሚወክል ኮፕ32 በማዘጋጀት ረገድ በጋራ ስለምንሰራባቸው መንገዶች ተወያይተናል” ብለዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ብሎም ዋና ፀሐፊው ከቡድናቸው ጋር በመሆን ኮፕ32 ስኬታማ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ እተማመናለሁ ሲሉም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የ2027 የአየር ንብረት ጉባኤ ለማዘጋጀት መመረጧ ይታወሳል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates