ዲፕሎማሲ

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር በስልክ ውይይት ማድረጋቸውን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታወቀ።።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 25/03/2018፡- የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ዋና ምክትል ቃል አቀባይ ቶሚ ፒጎት እንደገለጹት፣ የሁለቱ ባለስልጣናት ውይይት ትኩረቱን ያደረገው በቀጠናዊ መረጋጋት እና በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ነው።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እንደገለጸው፣ በውይይቱ ወቅት ሁለቱ ወገኖች አሜሪካ እና ኢትዮጵያ ለቀጠናው ሰላም እና መረጋጋት ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

በተለይም ውስብስብ የጂኦ-ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች በሚታዩበት የአፍሪካ ቀንድ፣ የሰላም መሰረትን ለመጣል እና ትብብርን ለማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸው ተገልጿል።

ይህ የስልክ ውይይት እና ከሰሞኑ ኢትዮጵያን ከጎበኙት የአሜሪካ አፍሪካ እዝ አዛዥ ጄነራል ዳግቪን አንደርሰን ጋር ተያያዞ፣ በአዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እና በጋራ ጉዳዮች ላይ ተቀራርቦ ለመስራት ያለመ መሆኑን ተገልጿል።

ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ፣ ሶማሊላንድ እና ፑንትላንድ የጎበኙት የአሜሪካ የአፍሪካ እዝ (AFRICOM) አዛዥ ሌተናንት ጄኔራል ዳግቪን አንደርሰን አሜሪካ በአይኤሲአይኤስ፣ በአልሸባብ እና በሌሎች የሽብር ቡድኖች ላይ ከፍተኛ ጫና ለማሳደር ያላትን ቁርጠኝነት ለማጠናከር እና ከቀጠናዊ አጋሮች ጋር በጋራ ፀጥታ ለማረጋገጥ ቅንጅት ለማጠናከር ያለመ እንደነበር መገለፁ ይታወሳል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates