አሜሪካ

ትራምፕ የሶማሊያ ስደተኞች “ወደመጡበት መመለስ አለባቸው” ሲሉ ዛቱ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 24/03/2018፡ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሶማሊያ ስደተኞች በአሜሪካ እንደማይፈልጉ በመግለጽ ለጋዜጠኞች “ወደመጡበት መመለስ አለባቸው” እና “አገራቸው ጥሩ ያልሆነው በምክንያት ነው” አሉ።

ማክሰኞ ዕለት በካቢኔ ስብሰባ ላይ “እውነቱን ለመናገር በአገራችን እንዲኖሩ አልፈልግም” ብለዋል። ትራምፕ “ወደ አገራችን ቆሻሻ መውሰድ ብንቀጥል አሜሪካ በተሳሳተ መንገድ ትሄዳለች” ብለዋል።

የኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት በሚኒሶታ ሰፊ የሶማሌ ማኅበረሰብ ውስጥ ዘመቻ እያቀዱ ስለመሆናቸው እየተነገረ ባለበት ነው ትራምፕ ይህን የሚያንኳስስ አስተያየት የሰጡት።

የሚኒሶታ ግዛት ባለሥልጣናት ዕቅዱ ከምሥራቅ አፍራዊቷ አገር የመጡ የሚመስሉ የአሜሪካ ዜጎችን ያለአግባብ ጠራርጎ ሊያስወጣ እንደሚችል በመግለጽ አውግዘዋል።

በጋራ ‘ትዊን ሲቲስ’ የሚባሉት ሚኒያፖሊስ እና ሴንት ፖል የተባሉት በዓለም ላይ ካሉት ትላልቅ የሶማሌ ማኅበረሰቦች መገኛ መካካል ናቸው። ከተሞቹ በአሜሪካ ውስጥ ትልልቆቹ የሶማሊ ማኅበረሰብ መገኛ ናቸው።

ትራምፕ ማክሰኞ ዕለት ለሰዓታት በቴሌቪዥን ከተላለፈ የካቢኔ ስብሰባ በኋላ በሰጡት አስተያየት “በአገራችን እንዲኖሩ አልፈልግም ብሏል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates