ዲፕሎማሲ

የሶማሊያ የመከላከያ ሚኒስትር ግብፅ በሶማሊያ የጦር ሰራዊት ለማሰማራት በምታደርገው ዝግጅት ለመወያየት ካይሮ መግባታቸው ተሰማ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 23/03/2018፡- የሶማሊያ የመከላከያ ሚኒስትር አህመድ ማካሊን ፊቂ ከአገሪቱ የጦር አዛዥ ጋር በመሆን ትላንት ወደ ግብፅ መጓዛቸው የተገለፀ ሲሆን በስትራቴጂካዊ ግንኙነቶች እና የቀጠናዊ ደህንነት ትብብርን ለማጠናከር ያለመ ከግብፅ የጦር አመራሮች ውይይት ማድረጋቸውን የመንግስት ምንጮች ገልጸዋል።

ጉብኝቱ የተደረገው ግብፅ በቂ ገንዘብ ያልተገኘለትን የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ #AUSSOM ለመደገፍ ወታደሮችን ወደ ሶማሊያ ለማሰማራት በዝግጅት ላይ ባለችበት ወቅት ነው።

በአፍሪካ ቀንድ የግብፅ ወታደራዊ ተሳትፎ በኢትዮጵያ ላይ ቀጠናዊ ተጽዕኖ ለመፍጠር የምታደርገው ሰፊ ስትራቴጂ አካል ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።

የሶማሊያ የመከላከያ ባለ ስልጣናት የጉዟቸው ትኩረት ወታደራዊ ትብብርን ማጠናከር እንደሆነ እየተገለፀ ነው።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates