ጤና

በኮንጎ 43 ሰዎች በኢቦላ ቫይረስ ሕይወታቸው ማለፉ ተነገረ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 23/03/2018፡- በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ጥረት እየተደረገ መሆኑን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

የሀገሪቱ ጤና ሚኒስትር ሮገር ካምባ 53 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ፣ 43 የሚሆኑት ህይወታቸው አልፏል ብለዋል።
ወረርሽኙ እንዳይስፋፋ ለመከላከል ከ27,000 በላይ ለሚደርሱ ዜጎች ክትባት ተሰጥቷል ተብሏል።

በመስከረም ወር፣ 2025 የኮንጎ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በካሳይ ግዛት የኢቦላ ወረርሽኝ መከሰቱን በይፋ አስታውቋል።

ከዚህ ጊዜ ጀምሮ 64 ሰዎች በኢቦላ ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን ከእነዚህ 45 መሞታቸው ተገልጿል።

በአሁኑ ጊዜ የኢቦላ በሽታ ከተጠቀሰው የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ወጪ ስርጭቱ እንደሌለ የአፍሪካ በሽታዎች ቁጥጥርና ክትትል ማእከል ያስታወቀ ሲሆን ቫይረሱ በአገሪቱ በ1976 ለመጀመሪያ ጊዜ ከታየ ጀምሮ ለ16ኛ ጊዜ መከሰቱ ገልጿል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates