ፖለቲካ
በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ ከ1,600 በላይ ሰላማዊ ሰዎች ከ ሱዳን ኮርዶፋን ግዛት እንደሸሹ ተመድ አስታወቀ።

ኢትዮ ሞ ኒተር፡ 22/03/2018፡- የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ጥቃቶች መጨመራቸውና የጸጥታ እጦት እየተባባሰ መምጣቱን ተከትሎ ከአንድ ቀን ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከ1,600 በላይ ሱዳናውያን በደቡብ ኮርዶፋን ግዛት ከምትገኘው ከርታላ ከተማ መሸሻቸውን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት አስታወቀ።
ተቋሙ ትናንት እሁድ እንዳስታወቀው የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በሚፈፅማቸው ጥቃቶች የጸጥታ ሁኔታው መባባሱን ተከትሎ 1,625 ሰዎች ህዳር 19/2018 ዓ.ም ከከርታላ ከተማ ለቀው ወጥተዋል ብሏል።
ተፈናቃዮቹ በዳላሚ አካባቢ በሚገኙ የተበተኑ ቦታዎች የሸሹ ሲሆን በአካባቢው ያለው ሁኔታ አሁንም ቢሆን የሰላም እጦት ያለበት መሆኑን ተመድ አስጠንቅቋል።
የሱዳን ጦር ከእሁድ ዕለት ቀደም ብሎ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል እና ከአጋሩ የሱዳን ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ ጋር ግጭት ውስጥ መግባቱን ተከትሎ በደቡባዊ ኮርዶፋን የሚገኘውን የአባሲያ ታጋሊን ምዕራባዊ ክፍሎች በቁጥጥሩ ስር ማዋሉን መረጃዎች ጠቁሟል።



