ኢኮኖሚ

በኢትዮጵያ የተከሰተው እሳተ ጎመራ ተከትሎ የተለያዩ አለም አቀፍ በረራዎች መሰረዛቸው ታወቀ፡፡

የእሳተ ጎመራው አመድ ብናኝ እስከ ህንድና ፓኪስታን መድረሱ እየተገለፀ ነው፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 16/03/2018፡- የህንድ እና አካሳ አየር መንገዶች በኢትዮጵያ በደረሰው የእሳተ ጎመራ ፍንዳታ ተከትሎ ወደ መካከለኛ ምስራቅ ሊያደርጉት የነበረው በረራ መሰረዛቸው አሳውቀዋል፡፡

የህንድ አየር መንገድ ዛሬ እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ የተከሰተው የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ምክንያት የተፈጠረው የአመድ ጭስ አንዳንድ በረራዎችን እንዲሰርዝ መገደዱ ገልፀዋል፡፡

የህንድ የአቪዬሽን ተቆጣጣሪ ለአየር መንገዶች በተሰጠው መመሪያ መሰረት ትላንትና ዛሬ ወደ መካከለኛ ምስራቅ ሊደረጉ የነበሩት 11 በረራዎች መሰረዙን አስታውቋል።

የተሰረዙ በረራዎቹ ወደ ጅዳ፣ ኩዌት እና አቡ ዳቢ የመሳሰሉ የመካከለኛው ምስራቅ መዳረሻዎች ታቅዶ የነበሩት መሆናቸው መረጃዎቹ አሳይተዋል።

በኢትዮጵያ ዓፋር ክልል ኤርታኢሌ አከባቢ ያጋጠመው የእሳተ ጎመራ ፍንዳታ ከአስር ሺዎች ዓመታት በኃላ የተከሰተ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የአመድ ብናኙ እስከ ህንድ፣ ፓኪስታን፣ እና ቀይ ባህርን ተሸግሮ መካከለኛ ምስራቅን እንደደረሰ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡

የሜትሮሎጂ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ፍንዳታው ወደ እስያ ክፍሎች ከመጓዙ በፊት ወደ ደቡብ ምስራቅ የመን እና ኦማን የሚንሳፈፉ ከፍተኛ ከፍታ ያላቸው አመድ ብናኞች መታየታቸውና የተለያዩ አገራት አየር መንገዶች የበረራ መንገዶችን ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አነሳስቷቸዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates