ዲፕሎማሲ

ኢትዮጵያ እና ሞሮኮ የፀጥታ ትብብር ስምምነት መፈራረማቸው ተሰማ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 16/03/2018፡- ኢትዮጵያ እና ሞሮኮ የፀጥታ ትብብራቸው ለማጠናከር የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን የሞሮኮ ብሔራዊ ደኅንነትና የግዛት ክትትል አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ_ፌዴራል_ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል እና የሞሮኮ ብሔራዊ ደኅንነትና የግዛት ክትትል ዋና ዳይሬክተር አብደላጢፍ ሀሙሺ በማራካሽ መካሄድ በጀመረው 93ኛው የኢንተርፖል ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን መፈራረማቸው ተገልፀዋል።

የስምምነቱ ዓላማ በሁለቱ አገራት የጥቃት ወንጀልን፣ የተደራጀ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀልን፣ የኮንትሮባንድ መረቦችን፣ ሕገወጥ ዝውውርን እና የሳይበር ወንጀልን በጋራ ለመዋጋት ነው ተብሏል።

ባሳለፍነው ዓመት ሰኔ ወር ኢትዮጵያ እና ሞሮኮ በጋራ ስልጠና፣ በልምምድ፣ በሳይንሳዊ ምርምር እና በወታደራዊ የጤና ፕሮግራሞች ላይ የመከላከያ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ያለመ የወታደራዊ ትብብር ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates