አፍሪካ

በአፍሪካ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚመሩ የሳይበር ጥቃቶች እየጨመሩ መምጣታቸውን አንድ ሪፖርት መለከተ።

ኢትዮሞኒር፡ 15/03/2018፡- አፍሪካ በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና በተፋጠነ ዲጂታላይዜሽን የተነሳ የሚፈፀሙባት የሳይበር ጥቃቶች በከፍተኛ ፍጥነት እየተባባሱ መምጣታቸውን ቼክ ፖይንት ሶፍትዌር ቴክኖሎጂስ በ2025 የአፍሪካ የሳይበር ደህንነት ባወጣው ሪፖርት አመለከተ።

ሪፖርቱ በአሁኑ ጊዜ በአፍሪካ ያሉ ድርጅቶች  በሳምንት በአማካይ ከ3 ሺህ በላይ የሳይበር ጥቃቶች እንደሚገጥማቸው አስታውቋል።

ከሀገራት መካከል ናይጄሪያ በብዛት ጥቃት ያስተናገደች ሲሆን፣ የናይጄሪያ ድርጅቶች በየሳምንቱ ከ4,200 በላይ ጥቃቶች ሲገጥሟቸው፣ የደቡብ_አፍሪካ ድርጅቶች ደግሞ ወደ 2,200 የሚጠጉ ጥቃቶችን ያስተናግዳሉ ብሏል ሪፖርቱ።

ድርጅቶች በወረቀት ላይ ከተመሠረተ አሠራር ወደ ዲጂታል ሥርዓቶች ሲሸጋገሩ እና የክላውድ አገልግሎቶችን መጠቀም ሲጀምሩ፣ ለሳይበር ጥቃት ተጋላጭ የመሆን ዕድሎች እየሰፋ በመሄድ ለጠላፊዎች በርካታ አጋጣሚዎችን እንደሚፈጥር ተገልጿል።

አክለውም ደህንነት በዲጂታል መፍትሔዎች እና በዲጂታላይዜሽን ሂደት ውስጥ መካተት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።
ሪፖርቱ በየሀገራቱ የሚፈፀሙ የሳይበር ጥቃት አላማቸውን አጉልቶ አሳይቷል።

ለአብነትም ደቡብ አፍሪካ በገንዘብ ተነሳሽነት ባላቸው ቡድኖች የሚፈጸሙ የ ‘ራንሰምዌር’ ጥቃቶች መጨመር የታየባት ሲሆን፤ እነዚህ ቡድኖች ለዝርፊያ ዓላማ በመረጃ ስርቆት ላይ ትኩረት ማድረጋቸው ተመላክቷል።

በሌላ በኩል፣ ኬንያ በአስፈላጊ የመሠረተ ልማት አውታሮች ላይ ጥቃቶች የገጠሟት ሲሆን፤ ከመንግሥት ጋር ግንኙነት ያላቸው ተዋናዮችን ኢላማ ያደረጉ ሊሆኑ እንደሚችሉ ሪፖርቱ ጠቁሟል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates