አፍሪካ

“የናንተ ወረቀት ተቀባይነት የለውም ብለን ነገረናቸዋል” ሲሉ የሱዳኑ ጄነራል አልቡርሃን ተናገሩ።

ኢትዮሞኒር፡ 15/03/2018፡- ጄኔራል አልብሩሀን በአሜሪካ የቀረበውን የሰላም ስምምነት ምክረ ሐሳብ እንደማይቀበሉትና በጦርነቱ እንደሚቀጥሉበት አስታውቀዋል፡፡

የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት መሪ ጄኔራል አብዱል ፈታህ አልብሩሀን በተቀናቃኛቸው ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ላይ የሚያካሂዱትን ወታደራዊ እርምጃ ለመቀጠል ዝግጁ መሆናቸውን ተናገሩ፡፡

ሱዳን ታይምስ እንደዘገበው ጄኔራሉ ይህንን የተናገሩት ትላንት በነጭ ናይል ግዛት አል ቁታይናህ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር ነው፡፡

እንደዘገባው የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትራምፕ ለሱዳን ጉዳይ ትኩረት እንደሚሰጡ ቃል በገቡ ማግስት ጄኔራሉ ለውይይት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀው የነበረ ቢሆንም የትላንቱ ንግግር ግን በቀናት ውስጥ ይህንን አቋማቸውን መቀየራቸውን የሚያሳይ ነው ተብሏል፡፡

በትራምፕ አስተዳደር ልዩ አማካሪ ሞሳድ ቦሎስ የቀረበውን አዲሱ የሰላም ውይይት እንደማይቀበሉት የገለፁት አልቡርሃን “የእናንተ ወረቀት ተቀባይነት የለውም ብለን ነግረናቸዋል” በማለት ዕቅዱ የኢሚሬትስ ፍላጎት የሚጭን ነው በማለት እንዳልተቀበሉት ገልጿል።

አሜሪካ፣ ግብፅ ሳውዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ኳድ በሚል ጥምረት የሱዳንን ጦርነት ለማስቆም ጥረት እያደረጉ ባሉበት ወቅት አልቡርሃን በግጭቱ እጃቸው ያለበት አገራት በመካተታቸው ዕቅዱ እንዳይቀበሉት እንዳደረጋቸው አብራርቷል።

የተባበሩት አረብ ኢሚሬትን የከሰሱት ጄነራሉ “እያደረግነው ያለነው የክብርና የሉአላዊነት ትግል ነው፤ ይህ እስኪረጋገጥና የጄነራል መሐመድ ዳጋሎ ሐይል እስኪደመሰስ ድረስ እንፋለማለን” ብሏል።

የጄኔራል አልብሩሀን ይህ የአቋም ለውጥ የመጣው በኤል ፋሻር ድል እያስመዘገቡ ባለበት ሲሆን ይሁን እንጂ ከፍተኛ ባለስልጣናቸው አስመራ ደርሰው ከተመለሱ በኋላ ነው እየተባለ ነው፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates