የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በተሻሻለው የደመወዝ ስኬል መክፈል እንዳልቻለ ገለፀ፡፡
ክልሉ በከባድ የበጀት ጉድለት ምክንያት አዲስ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ የደመወዝ ማስተካከያ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ አልቻልኩም ብለዋል፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 11/03/2018፡- የትግራይ ፕላን ኮሚሽን ክልሉ አዲሱን የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ የደመወዝ ማስተካከያ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ እንደማይችል በመግለጽ፣ ከፍተኛ የበጀት እጥረት በመኖሩ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የጨመረውን የደመወዝ ክፍያ ለመሸፈን የሚያስፈልገውን ሀብት ሳያገኝ ቀርቷል ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በነሐሴ ወር 2017 ዓ/ም የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የተሻሻለ የደመወዝ መለኪያ ማፅደቁ የሚታወስ ሲሆን፣ ይህም ከመስከረም ወር ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ ነበር።
ይሁን እንጂ የትግራይ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ሀንሳ ተክላይ እንዳሉት ክልሉ አዲሱን ማስተካከያ በአሰራር መስፈርቶች እና በዋና የገንዘብ ድጋፍ ክፍተት ምክንያት ወዲያውኑ ተግባራዊ ማድረግ አይችልም።
“እንደ አሰራር፣ የፌዴራል መንግስት ይህንን በሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ በፓርላማ እና በሌሎች አካላት ወስኗል። እዚህም ያንን አሰራር ማድረግ አለብን። ሆኖም በፌዴራል ደረጃ የተሰጡ ውሳኔዎችን ሁሉ በክልል ላይ መጫን አይችሉም” ብለዋል።
“ክልሉም በተመሳሳይ አሰራር ማለፍ አለበት – ለካቢኔው በማቅረብ ማፀደቅ፣ አዋጁን መተርጎም ይጠይቃል ያሉት ሐላፊዋ እና ይህም ጊዜ እንደሚጠይቅ አስረድተዋል፡፡
ኮሚሽነር ሀንሳ የትግራይ የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ መመሪያውን ተርጉሞ የራሱን ደንብ እንደረቀቀ በማብራራት፣ ይህም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ለክልል ካቢኔ ቀርቧል፤ ሆኖም በከፍተኛ የበጀት ጉድለት መተግባር አልተቻለም ብለዋል።
“ለዚህ አመት 12 ቢሊዮን ብር ይጠይቃል። የፌዴራል መንግስት የላከልን ግን 4.8 ቢሊዮን ብር ነው ያሉት ሃንሳ በዚህም ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ጉድለት አለብን፣ ይህን ያክል ሀብት ደግሞ እዚህ የለንም” ብለዋል።
ለሚቀጥሉት ሁለት ወራት መፍትሄ ለመስጠት መታቀዱንና፤ የሁለት ወር የደመወዝ ጭማሪ ለመክፈል ምወሰኑም ገልፀዋል።



