የተለያዩ

ኢትዮጵያ ከ98 ዓመታት በፊት የተወሰዱባት 12 ውድ ቅርሶች መመለስዋ ተገለፀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 11/03/2018፡- በ1920ዎቹ ከኢትዮጵያ የተወሰዱ 12 ውድ ቅርሶችን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናት እና ምርምር ተቋም መቀበሉን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቅዋል።

ቅርሶቹን የፕሮፌሰር ራሞን አያት እንዲሁም በ1920ዎቹ በኢትዮጵያ የጀርመን ልዑክ በነበሩት ፍራንዝ ዊስ የአገልግሎት ዘመን ከኢትዮጵያ የተወሰዱ ሲሆን፣ ፍራንዝ እና ባለቤታቸው ሄድዊግ ገንዘብ ከፍለው የሰበሰቧቸው ናቸው ተብሏል።

ለዩኒቨርሲቲው ከተበረከቱት ውድ ቅርሶች ውስጥ ዘውድ፣ ጋሻ፣ ጎራዴ፣ ዝናር፣ ስዕሎች እንዲሁም ከራስ ተፈሪ መኮንን የተበረከቱ ስጦታዎች እንደሚገኙበት ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

በመላው ዓለም በግለሰቦች እጅ እና በተቋማት ውስጥ የሚገኙና የኢትዮጵያ ታሪክ አስረጂ የሆኑ ጥንታዊ ቅርሶች ወደ ሃገር እንዲመለሱ የማድረጉ ጥረትም እንደሚቀጥልም ሚኒስቴሩ አስታውቀዋል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates