ጤና
የዓለም ጤና ድርጅት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለተከሰተው በሽታ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት 300 ሺ የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ መደረጉን አሳወቀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 05/03/2018፡- የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መግለጫ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተከሰተውን ቫይራል ሄሞራጂክ ፊቨር በሽታ አፋጣኝ ድጋፍ ለመስጠት ከአለም ጤና ድርጅት የአደጋ ጊዜ ፈንድ 300 ሺ የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ መደረጉን ይፋ አድርገዋል።
ዶ/ር ቴዎድሮስ የዓለም ጤና ድርጅት አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ሁሉ ድጋፍን ለማሳደግ ዝግጁ መሆኑንም አክለው ገልጸዋል።
መግለጫው ድንበር ዘለል የሆነ ስርጭትን ለመከላከል በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን የሚገኙ የዓለም ጤና ድርጅት ቢሮዎች በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን ጠቁሟል።
የዓለም ጤና ድርጅት በሽታው ወደ ተቀሰቀሰበት አካባቢ ባለሞያዎችን ጨምሮ የተለያዩ መድኃኒት እና ቁሳቁሶችን መላኩንም ዳይሬክተሩ አሳውቀዋል።



