የዓለም ገንዘብ ድርጅት ሰራተኞች በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉዞ ማጠናቀቃቸው ተገለፀ፡፡
ውይይቱም በሚቀጥሉት ሳምንታት በቨርቸዋል ቪድዮ እንደሚቀጥል ሰራተኞቹ ተናግረዋል።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 05/03/2018፡- በአልቫሮ ፒሪስ የሚመራው የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የሰራተኞች ቡድን በተራዘመው የብድር ተቋም ዙሪያ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ለአራተኛው ጊዜ የግምገማ ውይይት ካደረገ በኋላ ትላንት ህዳር 04 ቀን 2018 ዓ/ም ጉብኝታቸው ማጠናቀቃቸው ተገልፀዋል።
ተልዕኮው የተካሄደው እ.አ.አ. ከጥቅምት 30 እስከ ህዳር 13 በአዲስ አበባ መሆኑ ታውቀዋል። በጉብኝቱ መጨረሻ ላይ ሚስተር ፒሪስ ቡድኑ “በአራተኛው የተራዘመ የብድር ጉዳይ ግምገማ ላይ በሰራተኞች ደረጃ ጥሩ እድገት አሳይቷል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
“ውይይቶቹ በሚቀጥሉት ሳምንታት በምናባዊ/ቨርቸዋል መልኩ ይቀጥላሉ” ያሉት የቡድኑ መሪ የኢትዮጵያን ባለስልጣናት “ለሞቅ ያለ እንግዳ ተቀባይነታቸው እና ውጤታማ ውይይቶች” አመስግነዋል።
በተልእኮው ወቅት የድርጅቱ ቡድን ከፋይናንስ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ፣ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ እና ከሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር መወያየቱ ታውቀዋል። ቡድኑ ከባንኮች እና ከግል ኩባንያዎች ተወካዮች ጋርም ውይይት አድርጓል ተብለዋል።
“ጥቂት ያልተፈቱ ጉዳዮች ይቀራሉ” ሲሉ ሚስተር ፒሪስ ተጨማሪ ዝርዝሮችን ሳይሰጡ ገልጸው የተከታታይ ውይይቶች በምናባዊ መልኩ እንደሚቀጥሉ በድጋሚ ተናግረዋል።
የአይኤምኤፍ ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ በሐምሌ 2025 ከኢትዮጵያ ጋር የተደረገውን የ2025 የአንቀጽ IV ምክክር ከሦስተኛው የ48 ወራት የተራዘመ የብድር ተቋም ስምምነት ግምገማ ጋር አጠናቋል።
ውሳኔው የኢትዮጵያን የክፍያ ሚዛን እና የፋይናንስ ፍላጎቶች ለማሟላት 262.3 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወዲያውኑ እንዲከፈል አስችሏል።
የግምገማው መጠናቀቅ በስምምነቱ መሠረት አጠቃላይ ክፍያዎች ወደ 1.873 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንዲደርስ አድርጓል።
IMF በሐምሌ ሪፖርቱ ኢትዮጵያን ከፍተኛ ዕዳ ካላቸው የአፍሪካ አገሮች መካከል ማካተቱ ይታወሳል።



